ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊትንም፥ “ሂድ፤ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር” ብሎ በላያቸው አስነሣው።
2 ዜና መዋዕል 21:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ፍልስጥኤማውያንንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረብያን ሰዎች በኢዮራም ላይ አስነሣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ፍልስጥኤማውያንንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩ ዐረቦችን በኢዮራም ላይ በጠላትነት እንዲነሡ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም የፍልስጥኤማውያንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረባውያንን የቊጣ መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባሕር ዳርቻ ሰፍረው በነበሩት ኢትዮጵያውያን አጠገብ ፍልስጥኤማውያንና ዐረቦች ይኖሩ ነበር፤ እግዚአብሔርም እነርሱን በኢዮራም ላይ ጦርነት እንዲያደርጉ አነሣሣቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የፍልስጥኤማውያንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረባውያንን መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሣ። |
ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊትንም፥ “ሂድ፤ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር” ብሎ በላያቸው አስነሣው።
እግዚአብሔርም ሰሎሞንን አለው፥ “ይህን ሠርተሃልና፥ ያዘዝሁህንም ትእዛዜንና ሕጌን አልጠብቅህምና መንግሥትህን ከአንተ ከፍዬ ለባሪያህ እሰጠዋለሁ።
እግዚአብሔርም ኤዶማዊው አዴርን ከረምማቴር ወገን የኤልያዳሔ ልጅ ኤስሮምን የሲባ ንጉሥ ጌታውን አድረዓዛርን ጠላት አድርጎ በሰሎሞን ላይ አስነሣ። ሰዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ። የዓመፁም አበጋዝ እርሱ ነበር። ደማስቆንም እጅ አደረጋት። በሰሎሞንም ዘመን ሁሉ በእስራኤል ላይ ጠላት ሆነ። ኤዶማዊው አዴርም ከኤዶምያስ ነገሥታት ዘር ነበር።
እግዚአብሔርም ደግሞ ከጌታው ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር የኰበለለውን የኤልያዳን ልጅ ሬዞንን ጠላት አድርጎ አስነሣበት።
ከፍልስጥኤማውያንም ለኢዮሳፍጥ እጅ መንሻና የብር ግብር ያመጡ ነበር፤ ዐረባውያንም ደግሞ ከመንጎቻቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎችንና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየሎችን ያመጡለት ነበር።
በኢየሩሳሌምም የነበሩት ታናሹን ልጁን አካዝያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡት። የመጣባቸው የዓረብና የአሊማዞን የሽፍቶች ጭፍራ የእርሱን ታላቆች ወንድሞች ገድለዋቸው ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ።
ስለዚህም እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ሠራዊት አለቆች አመጣባቸው፤ ምናሴንም በዛንጅር ያዙት፤ በሰንሰለትም አስረው ወደ ባቢሎን ወሰዱት።
በኤርምያስ አፍ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ከተፈጸመ በኋላ በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፤ እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ አስነገረ፤ ደግሞም በጽሕፈት እንዲህ አለ፦
የይሁዳና የብንያም የአባቶች ቤቶች አለቆችም፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት ይወጡ ዘንድ እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው ሁሉ ተነሡ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በኤዶምያስ ይዘጉባቸው ዘንድ የሰሎሞንን ምርኮ ማርከዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጋዛ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይደነግጡምን? ወይስ እግዚአብሔር ያላዘዘው ክፉ ነገር በከተማ ላይ ይመጣልን?
አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእኔን የአገልጋይህን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አስነሥቶህ እንደሆነ፥ ቍርባንህን ይቀበል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ላይ እንዳልቀመጥ ዛሬ ጥለውኛልና በእግዚአብሔር ፊት ርጉማን ይሁኑ።