እነርሱ ተቀመጡባት፤ ለስምህም መቅደስን ሠሩባት።
እነርሱም ተቀመጡባት፤ ለስምህ መቅደስ ሠሩባት፤ እንዲህም አሉ፤
እነርሱም ተቀመጡባት፥ ለስምህም መቅደስን ሠርተውባት እንዲህ አሉ፦
ሕዝብህም በዚህች ምድር እስከ አሁን ይኖራል፤ ለአንተም ክብር ቤተ መቅደስን ሠርቶአል፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት፥
እነርሱም ተቀመጡባት፤ ለስምህም መቅደስን ሠርተውባት
እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን ለማጠን፥ የገጹንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በአምላካችንም በእግዚአብሔር በዓላት ለማቅረብ እኔ ልጁ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራለሁ፤ እርሱንም እቀድሳለሁ።
አምላካችን ሆይ፥ በዚህ ምድር የነበሩትን አሕዛብ ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት ያሳደድህ፥ ለወዳጅህም ለአብርሃም ዘር ለዘለዓለም የሰጠሃት አንተ አይደለህምን?
እንዲህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍርድ ሰይፍ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ እንቆማለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመከራችንም ወደ አንተ እንጮኻለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ።
እግዚአብሔርም የተናገረውን ቃል ፈጸመ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ በአባቴ በዳዊት ፋንታ ተተካሁ፤ በእስራኤልም ዙፋን ላይ ተቀመጥሁ፤ ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ሠራሁ።
እርሱ፦ ሕዝቤን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ከእስራኤል ነገድ በዚያ ለስሜ ቤት ይሠራበት ዘንድ ከተማን አልመረጥሁም። በሕዝቤ እስራኤል ላይም ይነግሥ ዘንድ ሰውን አልመረጥሁም።
ነገር ግን ስሜ በዚያ እንዲጠራባት ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ። በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ ብሎአል።
እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።