Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እርሱ፦ ሕዝ​ቤን ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ በዚያ ለስሜ ቤት ይሠ​ራ​በት ዘንድ ከተ​ማን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም። በሕ​ዝቤ እስ​ራ​ኤል ላይም ይነ​ግሥ ዘንድ ሰውን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ‘ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ፣ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ ይሠራበት ዘንድ ከማናቸውም የእስራኤል ነገድ ከተሞች አንድም አልመረጥሁም፤ ወይም የሕዝቤ የእስራኤል መሪ ይሆን ዘንድ ማንንም አልመረጥሁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ‘ህዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤት በዚያ እንዲሠራልኝ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ማንኛውንም ከተማ አልመረጥሁም፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ እንዲሆን ማንንም አልመረጥሁም፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ‘ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በስሜ ቤተ መቅደስ የሚሠራበት ስፍራ ከመላው የእስራኤል ምድር አንድም ከተማ፥ እንዲሁም ሕዝቤን እስራኤልን የሚመራ ማንንም ሰው አልመረጥኩም ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እርሱ ‘ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤት በዚያ ይሠራልኝ ዘንድ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ማንኛውንም ከተማ አልመረጥሁም፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ ማንንም አልመረጥሁም፤

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 6:5
25 Referencias Cruzadas  

ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ በእ​ር​ስ​ዋም ቤት ይሠ​ራ​ልኝ ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከተ​ማን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም፤ አሁን ግን ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ።”


ኀጢ​ኣት እንደ ምዋ​ር​ተ​ኝ​ነት ናትና አም​ል​ኮተ ጣዖ​ትም ደዌ​ንና ኀዘ​ንን ያመ​ጣል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ንቀ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ እን​ዳ​ት​ሆን ናቀህ” አለው።


ሳሙ​ኤ​ልም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “ከሕ​ዝቡ ሁሉ እር​ሱን የሚ​መ​ስል እንደ ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጠ​ውን ታያ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ንጉሥ ሕያው ይሁን” እያሉ እል​ልታ አደ​ረጉ።


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ በአ​ንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠ​ውን ስፍራ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ዚ​ያም ትመ​ጣ​ላ​ችሁ።


ራስ​ህን ጠብቅ፤ ስማው፤ እን​ቢም አት​በ​ለው፤ ስሜ በእ​ርሱ ስለ ሆነ ይቅር አይ​ል​ምና።


ከአ​ፈ​ርም መሠ​ዊያ ሥራ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን፥ በጎ​ች​ህ​ንም፥ በሬ​ዎ​ች​ህ​ንም ሠዋ​በት፤ ስሜን ባስ​ጠ​ራ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ መጥቼ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ።


እር​ሱም አለ፥ “ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት በአፉ የተ​ና​ገረ፥ በእ​ጁም የፈ​ጸመ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


ነገር ግን ስሜ በዚያ እን​ዲ​ጠ​ራ​ባት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ። በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ ብሎ​አል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ስሜን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ለሁ” ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መሠ​ዊ​ያን ሠራ።


ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድ​ን​ኳ​ንና በማ​ደ​ሪያ ኖርሁ እንጂ በቤት ውስጥ አል​ኖ​ር​ሁም።


ባሪ​ያህ በዚህ ቤት የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆ​ናል ወዳ​ል​ኸው ስፍራ፥ ወደ​ዚህ ቤት ዐይ​ኖ​ችህ ቀንና ሌሊት የተ​ገ​ለጡ ይሁኑ።


አሁ​ንም ስሜ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መር​ጫ​ለሁ፤ ቀድ​ሻ​ለ​ሁም፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም ዘወ​ትር በዚያ ይሆ​ናሉ።


ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸና፤ ንጉ​ሥም ሆነ፤ ሮብ​ዓ​ምም በነ​ገሠ ጊዜ የአ​ርባ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ያኖ​ር​ባት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ በመ​ረ​ጣት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የአ​ሞን ሴት ንዑማ ነበ​ረች።


እነ​ርሱ ተቀ​መ​ጡ​ባት፤ ለስ​ም​ህም መቅ​ደ​ስን ሠሩ​ባት።


እን​ዲ​ህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍ​ርድ ሰይፍ ወይም ቸነ​ፈር ወይም ራብ፥ ቢመ​ጣ​ብን በዚህ ቤት ፊትና በፊ​ትህ እን​ቆ​ማ​ለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመ​ከ​ራ​ች​ንም ወደ አንተ እን​ጮ​ኻ​ለን፥ አን​ተም ሰም​ተህ ታድ​ነ​ና​ለህ።


አሁ​ንም እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ አን​ገ​ታ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ስጡ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ወደ ተቀ​ደ​ሰው ወደ መቅ​ደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቍጣ​ው​ንም ከእ​ና​ንተ እን​ዲ​መ​ልስ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ስሜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል” ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የጣ​ዖት መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችን ሠራ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለዳ​ዊ​ትና ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን፥ “በዚህ ቤትና ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ በመ​ረ​ጥ​ኋት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስሜን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አኖ​ራ​ለሁ፤


በባ​ቢ​ሎ​ንም አው​ራጃ ሁሉ የም​ታ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ ሕዝ​ቡና ካህ​ና​ቱም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለው ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ቤት በፈ​ቃ​ዳ​ቸው የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትን ትወ​ስድ ዘንድ አዝ​ዘ​ዋል፤


እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ ሰይጣን ሆይ፥ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፣ በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን? አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios