La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 18:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ንጉ​ሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፥ “ሚክ​ያስ ሆይ፥ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ ልሂ​ድን? ወይስ ልቅር?” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ንጉሡ በመጣ ጊዜ ንጉሡ፣ “ሚክያስ ሆይ፤ በገለዓድ በምትገኘው ራሞት ላይ እንዝመት ወይስ እንቅር?” ሲል ጠየቀው። እርሱም መልሶ፣ “ሂዱና ድል አድርጉ፤ በእጃችሁ ዐልፈው ይሰጣሉና” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ንጉሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፦ “ሚክያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለጦርነት እንሂድን? ወይስ ልቅር?” አለው። እርሱም መለልሶ እንዲህ አለው፦ “ውጣ፥ ይከናወንልህ፤ በእጅህም ተላልፈው ይሰጣሉ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሚክያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ፊት በቀረበ ጊዜ ንጉሡ “ሚክያስ ሆይ፥ ንጉሥ ኢዮሣፍጥና እኔ ወደ ራሞት ሄደን ጦርነት እንክፈት? ወይስ እንተው?” ሲል ጠየቀው። ሚክያስም “ዝመትባት! በእርግጥም ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ንጉሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ “ሚክያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ እንሂድን? ወይስ እንቅር?” አለው። እርሱም “ውጣ፤ ተከናወን፤ በእጅህም አልፈው ይሰጣሉ” አለ።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 18:14
9 Referencias Cruzadas  

በቀ​ት​ርም ጊዜ ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ፥ “አም​ላክ ነውና በታ​ላቅ ቃል ጩኹ፤ ምና​ል​ባት ይጫ​ወት ይሆ​ናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆ​ናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀ​ስ​ቀስ ያስ​ፈ​ል​ገ​ዋል” እያለ ይዘ​ባ​በ​ት​ባ​ቸው ጀመር።


ወደ ንጉ​ሡም ደረሰ። ንጉ​ሡም፥ “ሚክ​ያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ እን​ሂ​ድን? ወይስ እን​ቅር?” አለው። እር​ሱም፥ “ውጣና ተከ​ና​ወን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በን​ጉሡ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታል” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤


ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አም​ላኬ የሚ​ለ​ውን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ።


ነቢዩ ሚክ​ያ​ስም፥ “ውጣ፤ ተከ​ና​ወን፤ በእ​ጅ​ህም አል​ፈው ይሰ​ጣሉ” አለ። ንጉ​ሡም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከእ​ው​ነት በቀር እን​ዳ​ት​ነ​ግ​ረኝ ስንት ጊዜ አም​ል​ሃ​ለሁ?” አለው።


እን​ጀ​ራ​ህን በውኃ ፊት ላይ ጣለው፥ ከብዙ ቀን በኋላ ታገ​ኝ​ኘ​ዋ​ለ​ህና።


ሣን። በዖፅ ምድር የም​ት​ኖሪ የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፥ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዋ ደግሞ ወደ አንቺ ያል​ፋ​ልና፥ አን​ቺም ትሰ​ክ​ሪ​አ​ለሽ፥ ትራ​ቆ​ቻ​ለ​ሽም።


ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ “እንግዲህስ ተኙ፤ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች፤ የሰው ልጅም በኀጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።