2 ዜና መዋዕል 16:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቱ በተሞላ አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የቀብር ሥርዐት አደረጉለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዳዊት ከተማ ከዐለት አስፈልፍሎ ለራሱ ባሠራውም መቃብር ቀበሩት። በቅመማ ቅመምና በልዩ ልዩ ጣፋጭ ሽቱዎች በተሞላ ቃሬዛ ላይ አኖሩት፤ ስለ ክብሩም ትልቅ እሳት አነደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቶ በተሞላው አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የመቃብር ወግ አደረጉለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሬሳውም በልዩ ቅመማ ቅመምና በሽቶ ታሽቶ እርሱ ራሱ በዳዊት ከተማ ከአለት አስፈልፍሎ ባሠራው መቃብር ተቀበረ፤ ስለ ክብሩም ብዙ እንጨት ከምረው በማንደድ ታላቅ ለቅሶ አደረጉለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቱ በተሞላው አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የመቃብር ወግ አደረጉለት። |
አባቴ ሳይሞት አምሎኛል፤ እንዲህ ሲል፦ ‘እነሆ እኔ እሞታለሁ፤ በቈፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር በዚያ ቅበረኝ።’ አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ።”
አሣሄልንም አንሥተው በቤተ ልሔም በአባቱ መቃብር ቀበሩት፤ ኢዮአብና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ፤ ሄዱ፥ በኬብሮንም አነጉ።
ከቀንም ወደ ቀን እንዲህ ሆነ፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀቱ ወጣ፤ በክፉም ደዌ ሞተ። ሕዝቡም ለአባቶቹ ያደርገው እንደ ነበረ ለእርሱ የመቃብር ወግ አላደረገም።
ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ልጆች መቃብር በላይኛው ክፍል ቀበሩት፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትም ሁሉ በሞቱ አከበሩት። ልጁም ምናሴ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
ብላቴኖቹም ከሰረገላው አውርደው ለእርሱ በነበረው በሁለተኛው ሰረገላ ውስጥ አስቀመጡት፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጡት፤ እርሱም በዚያ ሞተ፤ በአባቶቹም መቃብር ተቀበረ፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌምም ሁሉ ለኢዮስያስ አለቀሱ።
መቃብር በዚያ ያስወቀርህ፥ ከፍ ባለው ስፍራ መቃብር ያሠራህ፥ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖርያ ያሳነጽህ ወደዚህ ለምን መጣህ? ለምንስ በዚህ ተደፋፈርህ?
ነገር ግን በሰላም ትሞታለህ፥ ከአንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገሥታት አባቶችህ እሳት ይቃጠልላቸው እንደ ነበር እንዲሁ ያቃጥሉልሃልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ! እያሉ ያለቅሱልሃል፤ እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና” ይላል እግዚአብሔር።
የሳኦልንም ሬሳ፥ የልጁ የዮናታንንም ሬሳ ከቤትሶም ቅጥር ላይ አወረዱ፤ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በዚያም አቃጠሉአቸው።