የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ ይገደል ዘንድ ማሉ።
2 ዜና መዋዕል 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔርም በታላቅ ድምፅና በእልልታ፥ በእንቢልታና በቀንደ መለከት ማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህንም በታላቅ ድምፅ፣ በእልልታ፣ በእንቢልታና በመለከት ድምፅ ለእግዚአብሔር ማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታም በታላቅ ድምፅና በዕልልታ፥ እምቢልታንና ቀንደ መለከትንም እየነፉ ማሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የገቡትን ቃል ኪዳን የሚጠብቁ መሆናቸውንም በማረጋገጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በእግዚአብሔር ስም ማሉ፤ ከዚህም በኋላ በጥሩምባና በእምቢልታ ድምፅ ታጅበው በሆታና በእልልታ ደስታቸውን ገለጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔርም በታላቅ ድምፅና በዕልልታ፥ በእምቢልታና በቀንደ መለከት ማሉ። |
የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ ይገደል ዘንድ ማሉ።
በፍጹምም ልባቸው ምለዋልና፥ በፍጹምም ሕሊናቸው ፈልገውታልና፥ እርሱም ተገኝቶላቸዋልና ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው ዕረፍትን ሰጣቸው።
በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ፥ ፍርዱንም፥ ሥርዐቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ርግማንንና መሐላን አደረጉ።
ደግሞም ልብሴን አራገፍሁና፥ “ይህን ነገር የማያደርገውን ሰው ከቤቱና ከሥራው እንዲሁ እግዚአብሔር ያራግፈው፤ እንዲሁ የተራገፈና ባዶ ይሁን” አልሁ። ጉባኤውም ሁሉ፥ “አሜን” አሉ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ ሕዝቡም እንደዚህ ነገር አደረጉ።
ሙሴና አሮን በክህነታቸው ቅዱሳን ናቸውና ሳሙኤልም ስሙን ከሚጠሩት ጋራ፤ እግዚአብሔርን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።
ሙሴም ገባ፤ ለሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፥ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እንሰማለን፤ እናደርጋለንም” ብለው መለሱ።
የቃል ኪዳኑንም መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ አነበበላቸው፤ እነርሱም፥ “እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እንሰማለን፤ እናደርጋለንም” አሉ።