ገባዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበርና በዚያ መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ ተነሥቶ ሄደ፤ ሰሎሞንም በዚያ መሠዊያ ላይ በገባዖን አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዋ።
2 ዜና መዋዕል 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች ለመቶ አለቆችም፥ ለፈራጆችም፥ በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ሁሉ ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሰሎሞን ለመላው እስራኤል፣ ለሻለቆች፣ ለመቶ አለቆች፣ ለዳኞች፣ ለእስራኤል መሪዎች ሁሉ እንዲሁም ለየቤተ ሰቡ አለቆች ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለፈራጆችም፥ በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞን ለእስራኤላውያን ሁሉ፥ ለሺህ አለቆችና ለመቶ አለቆች፥ እንዲሁም ለመንግሥቱ ባለ ሥልጣኖች፥ ለቤተሰብ መሪዎችና ሕዝብ በሙሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለፈራጆችም፥ በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ። |
ገባዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበርና በዚያ መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ ተነሥቶ ሄደ፤ ሰሎሞንም በዚያ መሠዊያ ላይ በገባዖን አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዋ።
“እናንተ የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናችሁ፤ ወዳዘጋጀሁላት ስፍራ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ታመጡ ዘንድ እናንተና ወንድሞቻችሁ ተቀደሱ።
እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላላቆች እንደ ታናናሽ ወንድሞቻቸው፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ዐሥራ ስድስት አለቆች፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ።
የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆችና የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆችም ለንጉሡና ለንጉሡ ትእዛዝ ሁሉ የሚያገለግሉ ሹማምት እንደ ቍጥራቸው በየክፍላቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓመቱ ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር።
ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉና የፍርድ አለቆችን፥ ንጉሡንም በየተራ የሚጠብቁትን አለቆቹን፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሡና በልጆቹ ሀብትና ንብረት ላይ፥ መባ ባለበት ላይ የተሾሙትን ጃንደረቦችንም፥ ኀያላኑንና ሰልፈኞቹን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
ንጉሡ ዳዊትም ለጉባኤው ሁሉ እንዲህ አለ፥ “እግዚአብሔር ብቻውን የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ለጋ ብላቴና ነው፤ ሕንጻው ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክ ነው እንጂ ለሰው አይደለምና ሥራው ታላቅ ነው።
ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር የምስክር ድንኳን በዚያ ነበረና በገባዖን ወዳለው የኮረብታው መስገጃ ሄዱ።