Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 1:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ንጉሥ ሰሎሞን ለእስራኤላውያን ሁሉ፥ ለሺህ አለቆችና ለመቶ አለቆች፥ እንዲሁም ለመንግሥቱ ባለ ሥልጣኖች፥ ለቤተሰብ መሪዎችና ሕዝብ በሙሉ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከዚያም ሰሎሞን ለመላው እስራኤል፣ ለሻለቆች፣ ለመቶ አለቆች፣ ለዳኞች፣ ለእስራኤል መሪዎች ሁሉ እንዲሁም ለየቤተ ሰቡ አለቆች ተናገረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሰሎሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለፈራጆችም፥ በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ለሻ​ለ​ቆች ለመቶ አለ​ቆ​ችም፥ ለፈ​ራ​ጆ​ችም፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ዘንድ ለነ​በሩ መሳ​ፍ​ንት ሁሉ፥ ለአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ሁሉ ተና​ገረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሰሎሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለፈራጆችም፥ በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 1:2
13 Referencias Cruzadas  

ታላቅ መሠዊያ የሚገኘው በገባዖን ስለ ነበር አንድ ቀን ሰሎሞን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ፤ ከዚህም በፊት በዚያ መሠዊያ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦአል፤


ንጉሥ ዳዊት የሻለቅነትና የመቶ አለቅነት ማዕርግ ካላቸው የጦር አለቆች ጋር ተመካከረ፤


ሌዋውያኑንም እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ እናንተ ለሌዋውያን ጐሣዎች መሪዎች ናችሁ፤ የእስራኤል አምላክን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት እኔ ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ ተሸክማችሁ ታመጡ ዘንድ ራሳችሁንና ሌዋውያን ወገኖቻችሁን ሁሉ ቀድሱ፤


ስለዚህም ዳዊት የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደተዘጋጀለት ስፍራ ለመውሰድ የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም አስጠራ፤


የእያንዳንዱ ቤተሰብ አለቃና ታናሹ እንደ ታላቁ በእኩልነት ልክ ዘመዶቻቸው የአሮን ልጆች የነበሩት ካህናት ያደርጉት በነበረው ዐይነት ለሥራቸው ምድብ ዕጣ ይጥሉ ነበር፤ ንጉሥ ዳዊት፥ ሳዶቅ፥ አቤሜሌክና የካህናትና የሌዋውያን ቤተሰቦች አለቆች ሁሉ በተገኙበት ዕጣ ተጣጥለዋል።


የአልዓዛር ቤተሰብ ቊጥር ከኢታማር ቤተሰብ ቊጥር በልጦ ስለ ተገኘ አመዳደቡም በዚሁ መሠረት ተወሰነ፤ ስለዚህ የአልዓዛር የቤተሰብ አለቆች ቊጥር ዐሥራ ስድስት ሆኖ ሲደለደል የኢታማር አለቆች ቊጥር ስምንት እንዲሆን ወሰነ።


ከዚህ በታች የተመለከተው የእስራኤላውያን የቤተሰብ አለቆችና የጐሣ መሪዎች፥ እንዲሁም ዓመቱን በሙሉ በየወሩ ንጉሡንና ሕዝቡን የሚያገለግሉ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆችና አዛዦቻቸው ስም ዝርዝር ነው። እያንዳንዱ ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩት።


ንጉሥ ዳዊት የእስራኤል ባለ ሥልጣኖች በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው እንዲሰበሰቡ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ስለዚህ የየነገዱ መሪዎች፥ የመንግሥቱን ሥራ የሚያካሂዱ ባለሥልጣኖች የሻአለቆችና የመቶ አለቆች፥ የንጉሡንና የወንዶች ልጆቹን ንብረትና የቀንድ ከብት ተቈጣጣሪዎች እንዲሁም የቤተ መንግሥት ባለሟሎች፥ ዝነኞችና ታዋቂ የሆኑ ጀግኖች ሰዎች በሙሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።


ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ ሲል አስታወቀ፤ “እነሆ እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና የሥራ ልምድ የሌለው ነው፤ ይህ የሚሠራው ቤት፥ ቤተ መንግሥት ሳይሆን እግዚአብሔር አምላካችን የሚመለክበት ቤተ መቅደስ ስለ ሆነ መከናወን ያለበት ሥራ እጅግ ከባድ ነው።


በገባዖን ወደሚገኘው ኰረብታማ የማምለኪያ ስፍራ አብረውት እንዲሄዱ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ወደዚያ የሄዱበትም ምክንያት፥ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው፥ እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን በዚያው በገባዖን ስለሚገኝ ነው።


በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ የከተማይቱን ባለሥልጣኖች ሰብስቦ እነርሱን በማስከተል ወደ ቤተ መቅደሱ ሄደ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos