Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 29:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ንጉ​ሡም ሕዝ​ቅ​ያስ ማልዶ ተነሣ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት አለ​ቆች ሰበ​ሰበ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በማግስቱም ጧት በማለዳ፣ ንጉሥ ሕዝቅያስ የከተማዪቱን ሹማምት በአንድነት ሰብስቦ፣ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወጣ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ንጉሡም ሕዝቅያስ ማልዶ ተነሣ የከተማይቱንም አለቆች ሰበሰበ፥ ወደ ጌታም ቤት ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ የከተማይቱን ባለሥልጣኖች ሰብስቦ እነርሱን በማስከተል ወደ ቤተ መቅደሱ ሄደ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ንጉሡም ሕዝቅያስ ማልዶ ተነሣ የከተማይቱንም አለቆች ሰበሰበ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ወጣ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 29:20
8 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም ማልዶ ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ወሰደ፤ የውኃ አቍ​ማ​ዳ​ንም ለአ​ጋር በት​ከ​ሻዋ አሸ​ከ​ማት፤ ሕፃ​ኑ​ንም ሰጥቶ አስ​ወ​ጣት፤ እር​ስ​ዋም ሄደች፤ በዐ​ዘ​ቅተ መሐ​ላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በ​ዘች።


አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ።


ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ለሻ​ለ​ቆች ለመቶ አለ​ቆ​ችም፥ ለፈ​ራ​ጆ​ችም፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ዘንድ ለነ​በሩ መሳ​ፍ​ንት ሁሉ፥ ለአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ሁሉ ተና​ገረ።


ንጉ​ሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመ​ተ​ላ​ለፉ ያረ​ከ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል፤ ቀድ​ሰ​ና​ልም፤ እነ​ሆም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ሆነ​ዋል” አሉት።


ስለ መን​ግ​ሥ​ቱና ስለ መቅ​ደ​ሱም፥ ስለ ሕዝ​ቡም ስለ እስ​ራ​ኤል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሰባት ወይ​ፈ​ኖች፥ ሰባ​ትም አውራ በጎች፥ ሰባ​ትም የበግ ጠቦ​ቶች፥ ሰባ​ትም አውራ ፍየ​ሎች አመጡ። የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች ካህ​ና​ቱን፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ውጡ” አላ​ቸው።


ሙሴም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለ​ዳም ተነሣ፤ ከተ​ራ​ራ​ውም በታች መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለ​ትም ድን​ጋ​ዮ​ችን ለዐ​ሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ አቆመ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪ​ያ​ዎ​ቹን ነቢ​ያ​ትን ወደ እና​ንተ ላከ፤ እነ​ር​ሱም ማል​ደው ገሠ​ገሡ፤ እና​ን​ተም አል​ሰ​ማ​ች​ኋ​ቸ​ውም፤ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮ​አ​ች​ሁን አላ​ዘ​ነ​በ​ላ​ች​ሁም።


ኢያ​ሱም በማ​ግ​ሥቱ ማለዳ ተነሣ፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ጉን ታቦት ተሸ​ከሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos