Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ በም​ድረ በዳ የሠ​ራው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ስ​ክር ድን​ኳን በዚያ ነበ​ረና በገ​ባ​ዖን ወዳ​ለው የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የአምላክ የመገናኛ ድንኳን በዚያ ስለ ነበር፣ ሰሎሞንና መላው ጉባኤ በገባዖን ወዳለው ኰረብታ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር ጉባኤው ሁሉ የጌታ ባርያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው መገናኛ ድንኳን በዚያ ነበረና በገባዖን ወዳለው ወደ ኮረብታማው ስፍራ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በገባዖን ወደሚገኘው ኰረብታማ የማምለኪያ ስፍራ አብረውት እንዲሄዱ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ወደዚያ የሄዱበትም ምክንያት፥ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው፥ እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን በዚያው በገባዖን ስለሚገኝ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር ጉባኤው ሁሉ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር መገናኛ ድንኳን በዚያ ነበረና በገባዖን ወዳለው የኮረብታው መስገጃ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 1:3
12 Referencias Cruzadas  

ሙሴም በም​ድረ በዳ የሠ​ራት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያና ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በዚ​ያን ጊዜ በገ​ባ​ዖን ባለው በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ነበሩ።


ካህ​ኑን ሳዶ​ቅ​ንና ካህ​ና​ቱን ወን​ድ​ሞ​ቹን በገ​ባ​ዖን በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ፊት አቆ​ማ​ቸው፥


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በዚያ በሞ​ዓብ ምድር ሞተ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦


ደመ​ና​ውም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ከደነ፤ ድን​ኳ​ን​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ተሞ​ላች።


“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በፊ​ተ​ኛው ቀን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ትተ​ክ​ላ​ለህ።


በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ያሉት፥ ሥራ ሲሠሩ የነ​በ​ሩት በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ሁሉ ድን​ኳ​ኑን ከዐ​ሥር መጋ​ረ​ጃ​ዎች ሠሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊም፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ሠሩ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ በጥ​ልፍ ሥራ ኪሩ​ቤ​ልን አደ​ረ​ጉ​ባ​ቸው።


የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አመጡ።


ሰሎ​ሞ​ንም በገ​ባ​ዖን ካለው ኮረ​ብታ ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ነገሠ።


በገ​ባ​ዖን የሚ​ኖሩ ሰዎች ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​ያ​ሪ​ኮና በጋይ ያደ​ረ​ገ​ውን በሰሙ ጊዜ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios