1 ተሰሎንቄ 5:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማንኛውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ። |
በጽድቅ የሚሄድ፥ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በደልንና ኀጢአትን የሚጠላ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚያራግፍ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚደፍን፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ እውነትን ሁሉ፥ ቅንነትንም ሁሉ፥ ጽድቅንም ሁሉ፥ ንጽሕናንም ሁሉ፥ ፍቅርንና ስምምነትንም ሁሉ፥ በጎነትም ቢሆን፥ ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ አስቡ።
የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።