ዛሬም ወደ ውኃው ጕድጓድ መጣሁ፤ እንዲህም አልሁ፥ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የምሄድበትን መንገዴን ብታቀናልኝ፥
1 ሳሙኤል 9:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናውም፥ “እነሆ፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በዚህች ከተማ አለ፤ እርሱም የተከበረ ሰው ነው፤ የሚናገረው ሁሉ በእውነት ይፈጸማል፤ አሁንም ወደዚያ እንሂድ፤ ምናልባት የምንሄድበትን መንገድ ይነግረናልና” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዩ ግን፣ “እነሆ፤ በዚህች ከተማ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ፤ እርሱም በጣም የተከበረ ነው፤ የሚናገረውም ሁሉ በትክክል ይፈጸማል፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ይነግረን ይሆናልና ወደዚያ እንሂድ” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዩ ግን፥ “እነሆ፤ በዚህች ከተማ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ፤ እርሱም በጣም የተከበረ ነው፤ የሚናገረውም ሁሉ በትክክል ይፈጸማል፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ሊነግረን ይችል ይሆናልና ወደዚያ እንሂድ” ሲል መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዩም “ቈይ! እስቲ በዚህች ከተማ በጣም የተከበረ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ፤ እርሱ የሚናገረው ቃል ሁሉ በትክክል ይፈጸማል፤ ስለዚህም ወደ እርሱ እንሂድ፤ ምናልባትም አህዮቹን የት ማግኘት እንደምንችል እርሱ ሊነግረን ይችል ይሆናል” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ እነሆ፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በዚህች ከተማ አለ፥ እርሱም የተከበረ ሰው ነው፥ የሚናገረውም ሁሉ በእውነት ይፈጸማል፥ አሁን ወደዚያ እንሂድ፥ ምናልባት የምንሄድበትን መንገድ ይነግረናል አለው። |
ዛሬም ወደ ውኃው ጕድጓድ መጣሁ፤ እንዲህም አልሁ፥ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የምሄድበትን መንገዴን ብታቀናልኝ፥
ንጉሡም ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን፥ “እነሆ፥ አንተና ልጅህ አኪማኦስ፥ የአብያታርም ልጅ ዮናታን፥ ሁለቱ ልጆቻችሁ ከእናንተ ጋር በሰላም ወደ ከተማ ተመለሱ።
እነሆም፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በእግዚአብሔር ቃል ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤ ኢዮርብዓምም መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር።
ኤልሳዕም የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን እንደ ቀደደ በሰማ ጊዜ፥ “ልብስህን ለምን ቀደድህ? ንዕማን ወደ እኔ ይምጣ፤ በእስራኤልም ዘንድ ነቢይ እንዳለ ያውቃል” ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ።
የእግዚአብሔርም ሰው፥ “የወደቀው ወዴት ነው?” አለ፤ ስፍራውንም አሳየው፤ ከእንጨትም ቅርፊት ቀርፎ በዚያ ጣለው፤ ብረቱም ተንሳፈፈ።
የባርያውን ቃል ያጸናል፤ የመልእክተኞቹንም ምክር ይፈጽማል። ኢየሩሳሌምን፦ የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፤ የይሁዳንም ከተሞች ትታነጻላችሁ፤ ምድረ በዳዎችዋም ይለመልማሉ፤” ይላል፤
የእግዚአብሔርም ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በግብፅ በፈርዖን ቤት ባሪያዎች ሳሉ ለአባትህ ቤት ተገለጥሁ፤
ብላቴናው ደግሞ ለሳኦል መልሶ፥ “እነሆ፥ በእጄ የብር ሰቅል ሩብ አለኝ፤ እርሱንም ለእግዚአብሔር ሰው ትሰጠዋለህ፤ የምንሄድበትን መንገድም ይነግረናል።