አብርሃምም ወደ ብላቴኖቹ ተመለሰ፤ ተነሥተውም ወደ ዐዘቅተ መሐላ አብረው ሄዱ፤ አብርሃምም በዐዘቅተ መሐላ ተቀመጠ።
1 ሳሙኤል 8:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልጆቹም ስሞች እነዚህ ነበሩ። የበኵር ልጁ ስም ኢዩኤል፥ የሁለተኛውም ስም አብያ ነበረ። እነርሱም በቤርሳቤህ ፈራጆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበኵር ልጁ ኢዮኤል ሲሆን፣ ሁለተኛው ልጁ አብያ ነበረ፤ እነርሱም በቤርሳቤህ ይፈርዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበኩር ልጁ ስም ኢዩኤል ሲሆን፥ የሁለተኛው ልጁ ስም አቢያ ነበረ፤ እነርሱም በቤርሳቤህ ይፈርዱ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበኲር ልጁ ኢዩኤል፥ ታናሽ ልጁ አቢያ ተብለው የሚጠሩ ሲሆኑ በቤርሳቤህ ዳኞች ሆነው ተሾመው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበኩር ልጁም ስም ኢዮኤል፥ የሁለተኛውም ስም አብያ ነበረ። እነርሱም በቤርሳቤህ ይፈርዱ ነበር። |
አብርሃምም ወደ ብላቴኖቹ ተመለሰ፤ ተነሥተውም ወደ ዐዘቅተ መሐላ አብረው ሄዱ፤ አብርሃምም በዐዘቅተ መሐላ ተቀመጠ።
እስራኤልም ለእርሱ ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፤ ወደ ዐዘቅተ መሐላም መጣ፤ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ።
ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፤ ወደ ጌልገላም አትሂዱ፤ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ።”