ወንድሜን ሃናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያንም በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
1 ሳሙኤል 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን በእስራኤል ላይ ፈራጆች አድርጎ ሾማቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ፣ ልጆቹን ፈራጆች አድርጎ በእስራኤል ላይ ሾማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን ፈራጆች አድርጎ በእስራኤል ላይ ሾማቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ሁለቱን ልጆቹን በእስራኤል ላይ ፈራጆች አድርጎ ሾሞአቸው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን በእስራኤል ላይ ፈራጆች አደረጋቸው። |
ወንድሜን ሃናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያንም በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ ማዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።
በሠላሳ ሁለት የአህያ ግልገሎች ይቀመጡ የነበሩ ሠላሳ ሁለት ልጆችም ነበሩት፤ ለእነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች የተባሉ በገለዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተሞች ነበሩአቸው።
አርባም ልጆች፥ ሠላሳም የልጅ ልጆች ተወለዱለት፤ በሰባም የአህያ ግልገሎች ላይ ይቀመጡ ነበር። እስራኤልንም ስምንት ዓመት ገዛ።
አሁንም እነሆ፥ ንጉሡ በፊታችሁ ይሄዳል፤ እኔም አርጅቻለሁ፤ እንግዲህም አርፋለሁ፤ እነሆም፥ ልጆቼ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔም ከሕፃንነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊታችሁ ሄድሁ።