1 ሳሙኤል 7:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በመሴፋና በአሮጌው ከተማ መካከል አኖረው፤ ስሙንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድኤት ማለት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው፤ ስሙንም “እግዚአብሔር እስከ አሁን ድረስ ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዘር” ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው፤ “ጌታ እስከ አሁን ድረስ ረድቶናል” ሲል ስሙን “አቤንኤዘር” ብሎ ጠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል ተከለው፦ እግዚአብሔር እስካሁን ረድቶናል ለማለት ስሙን አቤንዔዜር ብሎ ሰየመው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፥ ስሙንም፦ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው። |
ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ሐውልት ተከለ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፤ ዘይትንም አፈሰሰበት።
ስሙ ለዘለዓለም ቡሩክ ነው፥ ከፀሓይም አስቀድሞ ስሙ ነበረ፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ፥ ሕዝቡ ሁሉ ያመሰግኑታል።
በዚያ ቀን በግብፅ ምድር መካከል አንዲቱ ከተማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ትሆናለች፤ በዳርቻዋም ለእግዚአብሔርዐምድ ይሆናል።
እግዚአብሔርም አዳነኝና ለታላቁም፥ ለታናሹም እየመሰከርሁ እስከ ዛሬ ደረስሁ፤ ይደረግ ዘንድ ካለው፥ ነቢያት ከተናገሩት፥ ሙሴም ከተናገረው ሌላ ያስተማርሁት የለም።
ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።
በእነዚያም ወራት እንዲህ ሆነ። ፍልስጥኤማውያን ለጦርነት በእስራኤላውያን ላይ ተሰበሰቡ። እስራኤልም ሊዋጉአቸው ወጡ፤ በአቤኔዜር አጠገብም ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንም በአፌቅ ሰፈሩ።