1 ሳሙኤል 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፤ ክፉም ነገር አመጣችባቸው፤ በእነርሱም ላይ በመርከቦች ውስጥ ወጣ፤ የአዛጦንንና የአውራጃዎችዋንም ሰዎች የውስጥ አካላቸውን በዕባጭ መታ፤ በከተሞቻቸውም መካከል አይጦች ወጡ፤ በከተማውም ታላቅ መቅሠፍት ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር እጅ በአሽዶድ ሕዝብና በአካባቢዋ ላይ ጠነከረ፤ እርሱም ጥፋት አመጣባቸው፤ በዕባጭም መታቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ እጅ በአሸዶድ ሕዝብና በአካባቢዋ ላይ ጠነከረ፤ እርሱም ጥፋት አመጣባቸው፤ በዕባጭም መቅሠፍት መታቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም የአሽዶድን ሕዝብ በብርቱ አስጨነቃቸው፤ እነርሱንና በዙሪያቸው ያሉትን ሕዝብ ሁሉ በእባጭ መቅሠፍት ቀጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፥ አጠፋቸውም፥ አዛጦንንና ድንበራቸውንም በእባጭ መታቸው። |
እነሆ፥ የእግዚአብሔር እጅ በሜዳ ውስጥ በአሉት በከብቶችህ፥ በፈረሶችም፥ በአህዮችም፥ በግመሎችም፥ በበሬዎችም፥ በበጎችም ላይ ትሆናለች፤ ይኸውም እጅግ ጽኑዕ ሞት ነው፤
እነሆ፥ አሁን የእግዚአብሔር እጅ በአንተ ላይ ነው፤ ዕውርም ትሆናለህ፤ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” ወዲያውኑም ታወረ፤ ጨለማም ዋጠው፤ የሚመራውም ፈለገ።
ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱአት፤ እኛንና ሕዝባችንን እንዳትገድል በስፍራዋ ትቀመጥ” አሉ።
የአዛጦንም ሰዎች እንዲህ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክራለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አትቀመጥ” አሉ።
ከሄደችም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ መጣች፤ ታላቅ ሁከትም ሆነ፤ የከተማዪቱንም ሰዎች ታላቁንም ታናሹንም መታ፤ የውስጥ አካላቸውንም በእባጭ መታቸው፤ የጌት ሰዎችም የውስጥ አካላቸውን ምስል ሠሩ፥