Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከሄ​ደ​ችም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ላይ መጣች፤ ታላቅ ሁከ​ትም ሆነ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሰዎች ታላ​ቁ​ንም ታና​ሹ​ንም መታ፤ የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ው​ንም በእ​ባጭ መታ​ቸው፤ የጌት ሰዎ​ችም የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን ምስል ሠሩ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱት በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በዕባጭ መታ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱትም በኋላ የጌታ እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በእባጭ መቅሠፍት መታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ነገር ግን የቃል ኪዳኑ ታቦት እዚያ ከደረሰ በኋላ እግዚአብሔር ያቺንም ከተማ ጭምር ቀጣ፤ ሕዝብዋንም በብርቱ አስጨነቀ። ሕፃኑንም ሽማግሌውንም ሳይለይ ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት በእብጠት በሽታ ቀጣቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከተሸከሙትም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በታላቅ ድንጋጤ በከተማይቱ ላይ ሆነች፥ ከታናሹም እስከ ታላቁ ድረስ የከተማይቱን ሰዎች መታ፥ እባጭም መጣባቸው።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 5:9
11 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በአ​ዛ​ጦን ሰዎች ላይ ከበ​ደች፤ ክፉም ነገር አመ​ጣ​ች​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ በመ​ር​ከ​ቦች ውስጥ ወጣ፤ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንና የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋ​ንም ሰዎች የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን በዕ​ባጭ መታ፤ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም መካ​ከል አይ​ጦች ወጡ፤ በከ​ተ​ማ​ውም ታላቅ መቅ​ሠ​ፍት ሆነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አዋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ዳግ​መ​ኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስ​ራ​ኤል ድን​በር አል​ወ​ጡም፤ በሳ​ሙ​ኤ​ልም ዘመን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ነበ​ረች።


ከሰ​ፈ​ርም መካ​ከል ተለ​ይ​ተው እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በላ​ያ​ቸው ነበረ።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ላይ ብታ​ምፁ፥ በእ​ና​ን​ተና በን​ጉ​ሣ​ችሁ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ትመ​ጣ​ለች።


ከአ​ን​በሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እን​ዳ​ገ​ኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግ​ድ​ግዳ ላይ እን​ዳ​ስ​ደ​ገ​ፈና እባብ እንደ ነደ​ፈው ሰው ይሆ​ናል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት፥ የወ​ርቁ አይ​ጦ​ችና የአ​ካ​ላ​ቸው እባ​ጮች ምሳሌ ያሉ​በ​ት​ንም ሣጥን በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ጫኑ።


ልከ​ውም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች ሁሉ ሰብ​ስ​በው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ታቦት ስደ​ዱ​አት፤ እኛ​ንና ሕዝ​ባ​ች​ንን እን​ዳ​ት​ገ​ድል በስ​ፍ​ራዋ ትቀ​መጥ” አሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና ላኩ​አት። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና በመ​ጣች ጊዜ አስ​ቀ​ሎ​ና​ው​ያን፥ “እኛ​ንና ሕዝ​ባ​ች​ንን ልታ​ስ​ገ​ድ​ሉን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ታቦት ለምን አመ​ጣ​ች​ሁ​ብን?” ብለው ጮኹ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios