ጽኑዓን ሰዎች ሁሉ ከገለዐድ ተነሥተው የሳኦልን ሬሳ የልጆቹንም ሬሳዎች ወሰዱ፥ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በኢያቢስም ካለው ከትልቁ ዛፍ በታች አጥንቶቻቸውን ቀበሩ፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።
1 ሳሙኤል 31:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልንም ሬሳ፥ የልጁ የዮናታንንም ሬሳ ከቤትሶም ቅጥር ላይ አወረዱ፤ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በዚያም አቃጠሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጀግኖቻቸው ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሙሉ ተጓዙ፤ የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ከቤትሳን ግንብ ላይ አውርደው ወደ ኢያቢስ አምጥተው አቃጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጀግኖቻቸው ሁሉ በሌሊት ወደ ቤትሻን ሄዱ። የሳኦልንና የልጆቹንም ሬሳ ከግንቡ ላይ አውርደው ወደ ያቤሽ አምጥተው አቃጠሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጀግኖቻቸው በድንገት ተነሥተው በመገሥገሥ በሌሊት ወደ ቤትሻን ሄዱ፤ የሳኦልንና የልጆቹን አስከሬን ከከተማይቱ ቅጽር ግንብ ላይ አውርደው ወደ ያቤሽ በማምጣት አቃጠሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጀግኖች ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ፥ የሳኦልንም ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ከቤትሳን ቅጥር ላይ አወረዱ፥ ወደ ኢያቢስም መጡ፥ በዚያም አቃጠሉት። |
ጽኑዓን ሰዎች ሁሉ ከገለዐድ ተነሥተው የሳኦልን ሬሳ የልጆቹንም ሬሳዎች ወሰዱ፥ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በኢያቢስም ካለው ከትልቁ ዛፍ በታች አጥንቶቻቸውን ቀበሩ፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።
ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቱ በተሞላ አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የቀብር ሥርዐት አደረጉለት።
ነገር ግን በሰላም ትሞታለህ፥ ከአንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገሥታት አባቶችህ እሳት ይቃጠልላቸው እንደ ነበር እንዲሁ ያቃጥሉልሃልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ! እያሉ ያለቅሱልሃል፤ እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና” ይላል እግዚአብሔር።
አጥንቶቻቸውንም ከቤት ያወጡ ዘንድ ቤተሰቦቻቸው በወሰዱአቸው ጊዜ፥ ቤት ጠባቂውን በአንተ ዘንድ የቀረ አለን? በአለው ጊዜ እርሱ የለም ይላል። ያም የእግዚአብሔርንም ስም እንዳትጠራ ዝም በል ይለዋል።