ከወደድኸኝስ ይህችን ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል፤ እግዚአብሔር ራርቶልኛልና፥ ለእኔም ብዙ አለኝና።” እስኪቀበለውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀበለውም።
1 ሳሙኤል 30:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ሴቄላቅ በመጣ ጊዜ ለይሁዳ ሽማግሌዎችና ለወዳጆቹ፥ “እነሆ፥ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ምርኮ በረከትን ተቀበሉ” ብሎ ከምርኮው ላከላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ወደ ጺቅላግ በመጣ ጊዜ፣ ወዳጆቹ ለሆኑት ለይሁዳ ሽማግሌዎች፣ “ከእግዚአብሔር ጠላቶች የተገኘ ስጦታ እነሆ፤” በማለት ከምርኮው ላይ ከፍሎ ላከላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ወደ ጺቅላግ በመጣ ጊዜ፥ ወዳጆቹ ለሆኑት ለይሁዳ ሽማግሌዎች፥ “ከጌታ ጠላቶች የተማረከ ስጦታ እነሆ ይሄው፤” በማለት ከምርኮው ላይ ከፍሎ ላከላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ወደ ጺቅላግ በተመለሰ ጊዜ ከምርኮው ከፊሉን ወዳጆቹ ለሆኑት ለይሁዳ ሽማግሌዎች ላከላቸው፤ ከላከላቸውም ምርኮ ጋር “ይህ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ተወስዶ የተላከላችሁ ስጦታ ነው” የሚል መልእክት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደ ጺቅላግ በመጣ ጊዜ ለዘመዶቹ ለይሁዳ ሽማግሌዎች፦ እነሆ፥ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ምርኮ በረከትን ተቀበሉ ብሎ ከምርኮው ሰደደላቸው። |
ከወደድኸኝስ ይህችን ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል፤ እግዚአብሔር ራርቶልኛልና፥ ለእኔም ብዙ አለኝና።” እስኪቀበለውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀበለውም።
እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ ኤልሳዕ ተመለሰ፤ ወደ እርሱም ደርሶ በፊቱ ቆመና፥ “እነሆ፥ በእስራኤል ነው እንጂ በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ ዐወቅሁ፤ አሁንም ከአገልጋይህ በረከት ተቀበል” አለው።
ስለዚህም አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው በቅድሚያ የተናገራችኋትን በረከታችሁን እንዲያዘጋጁ ወንድሞችን ማለድሁ፤ እንደዚህም የተዘጋጀ ይሁን፤ በረከትን እንደምታገኙበት እንጂ በንጥቂያ እንደ ተወሰደባችሁ አይሁን።
ሳኦልም ዳዊትን፥ “ታላቂቱ ልጄ ሜሮብ እነኋት፤ እርስዋን እድርልሃለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁንልኝ፤ ስለ እግዚአብሔርም ጦርነት ተጋደል” አለው። ሳኦልም፥ “የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእርሱ ላይ አትሁን” ይል ነበር።
እግዚአብሔር ለጌታዬ የታመነ ቤትን ይሠራለታልና፥ የጌታዬንም ጦርነት እግዚአብሔር ይዋጋለታልና የእኔን የባሪያህን ኀጢኣት፥ እባክህ፥ ይቅር በል፤ በዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህም።