1 ሳሙኤል 30:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንስ ነገር ማን ይሰማችኋል? እናንተ ከእነርሱ አትበልጡምና ወደ ጦርነት በሄዱት ድርሻ ልክ ጓዝ የጠበቁ ሰዎች ድርሻ እንዲሁ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትሉትን ማን ይቀበላችኋል? ከጓዝ ጋራ የቀረው ሰው ድርሻ ለጦርነት ከወጣው ሰው ድርሻ ጋራ አይበላለጥም፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምትሉትን ማን ይቀበላችኋል? ከጓዝ ጋር የቀረው ሰው ድርሻ ለጦርነት ከወጣው ሰው ድርሻ ጋር አይበላለጥም፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በምትሉት ነገር ማንም አይስማማበትም! ወደ ኋላ ቀርቶ ጓዝ ሲጠብቅ የቈየውም ሆነ ወደ ጦርነት የዘመተው ሁሉም የተገኘውን ምርኮ እኩል መካፈል አለበት” ሲል መለሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንስ ነገር ምን ይሰማችኋል? ነገር ግን የተዋጉትና ዕቃውን የጠበቁት እድል ፈንታ እኩል ይሆናል፥ አንድነት ይካፈላሉ አለ። |
“በብዙ ብልጥግና፥ በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”
የተጨነቀም ሁሉ፥ ዕዳም ያለበት ሁሉ፥ የተከፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰባሰበ፤ እርሱም በላያቸው አለቃ ሆነ፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ።
ዳዊትም ሰዎቹን፥ “ሁላችሁ ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም ሰይፉን ታጠቀ፤ አራት መቶ ሰዎችም ዳዊትን ተከትለው ወጡ፤ ሁለት መቶውም በጓዛቸው ዘንድ ተቀመጡ።
ዳዊትም አለ፥ “እግዚአብሔር አሳልፎ ከሰጠን በኋላ እንዲህ አታድርጉ፤ እርሱ ጠብቆናል፤ በእኛም ላይ የመጡትን ሠራዊት በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል፤