አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
1 ሳሙኤል 30:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች፥ ከወሰዱት ምርኮ ሁሉ፥ ታላቅም ሆነ፥ ታናሽም ሆነ፥ ምንም የተወላቸው የለም፤ ዳዊትም ሁሉን አስጣለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆች፣ ምርኮም ሆነ ሌላ፣ አማሌቃውያን ከወሰዱት ነገር ምንም የጐደለ አልነበረም፤ ዳዊት ሁሉንም አስመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትንሽም ሆነ ትልቅ፥ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆች፥ ምርኮም ሆነ ሌላ፥ አማሌቃውያን ከወሰዱት ነገር ምንም የጐደለ አልነበረም። ዳዊት ሁሉንም አስመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድም የጐደለ ሳይኖር ዳዊት የተከታዮቹን ወንዶችና ሴቶች ልጆች፥ እንዲሁም ዐማሌቃውያን ማርከው የወሰዱትን ምርኮ ሁሉ አስመለሰ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች፥ ከወሰዱትም ምርኮ ሁሉ፥ ታላቅም ሆነ ታናሽም ሆነ፥ ምንም የጎደለባቸው የለም፥ ዳዊትም ሁሉን አስጣለ። |
አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
ዳዊትም፥ “የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እርሱም፥ “ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮኞቹን ታድናለህና ፍለጋቸውን ተከተል” ብሎ መለሰለት።