Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 30:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 አንድም የጐደለ ሳይኖር ዳዊት የተከታዮቹን ወንዶችና ሴቶች ልጆች፥ እንዲሁም ዐማሌቃውያን ማርከው የወሰዱትን ምርኮ ሁሉ አስመለሰ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆች፣ ምርኮም ሆነ ሌላ፣ አማሌቃውያን ከወሰዱት ነገር ምንም የጐደለ አልነበረም፤ ዳዊት ሁሉንም አስመለሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ትንሽም ሆነ ትልቅ፥ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆች፥ ምርኮም ሆነ ሌላ፥ አማሌቃውያን ከወሰዱት ነገር ምንም የጐደለ አልነበረም። ዳዊት ሁሉንም አስመለሰ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ከወ​ን​ዶ​ችና ከሴ​ቶች ልጆች፥ ከወ​ሰ​ዱት ምርኮ ሁሉ፥ ታላ​ቅም ሆነ፥ ታና​ሽም ሆነ፥ ምንም የተ​ወ​ላ​ቸው የለም፤ ዳዊ​ትም ሁሉን አስ​ጣለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች፥ ከወሰዱትም ምርኮ ሁሉ፥ ታላቅም ሆነ ታናሽም ሆነ፥ ምንም የጎደለባቸው የለም፥ ዳዊትም ሁሉን አስጣለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 30:19
8 Referencias Cruzadas  

እርሱ አንተን የሚፈራህ እርሱንና ልጆቹን፥ ያለውንም ንብረት ሁሉ በደኅና ስለ ጠበቅህለት፥ የሚሠራውንም ሁሉ ስለ ባረክህለትና ብዙ የከብት መንጋ ስለ ሰጠኸው አይደለምን?


“እኛ አገልጋዮችህ፥ በእኛ ትእዛዝ ሥር የነበሩትን ወታደሮች ሁሉ ቈጥረናል፤ ከእነርሱ አንድም የጐደለ የለም።


እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤


የከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎችንም ሁሉ አገኘ፤ ተከታዮቹም እንስሶቹን በፊታቸው እየነዱ “ይህ ሁሉ የዳዊት ምርኮ ነው!” አሉ።


ዳዊትም “እነዚያን ወራሪዎች ተከታትዬ በማሳደድ ልያዛቸውን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “ተከተላቸው! እነርሱንም ይዘህ ምርኮኞችን በመታደግ ታድናለህ” ሲል መለሰለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos