ከአመለጡትም አንድ ሰው መጣ፤ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፤ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊው የመምሬ ዛፍ ይኖር ነበር፤ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።
1 ሳሙኤል 29:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፍልስጥኤማውያን አለቆች፥ “እነዚህ በኋላ የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አሉ፤ አንኩስም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች፥ “ይህ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ ዳዊት ነው፤ እርሱ በእነዚህ ሁለት ዓመታት ከእኛ ጋር ነበረ፤ ወደ እኔም ከተጠጋበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ምንም አላገኘሁበትም” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፍልስጥኤም አዛዦችም፣ “እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን እያደረጉ ነው?” ብለው ጠየቁ። አንኩስም፣ “ይህ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ የነበረው ዳዊት አይደለምን? ከእኔ ጋራ መኖር ከጀመረ እነሆ ዓመት ዐለፈው፤ እኔን ከተጠጋበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ምንም በደል አላገኘሁበትም” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፍልስጥኤም ጦር አዛዦችም እነርሱን ባዩ ጊዜ “እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ይሠራሉ?” ሲሉ ጠየቁ፤ አኪሽም፥ “ይህ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ የነበረው ዳዊት አይደለምን? ከእኔ ጋር መኖር ከጀመረ እነሆ ዓመት አለፈው፤ እኔን ከተጠጋበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ምንም በደል አላገኘሁበትም” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፍልስጥኤም ጦር አዛዦችም እነርሱን ባዩ ጊዜ “እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ይሠራሉ?” ሲሉ ጠየቁ። አኪሽም “ይህማ የእስራኤል ንጉሥ ባለሟል የነበረው ዳዊት አይደለምን? እነሆ እርሱ ከእኔ ጋር ሲኖር ብዙ ጊዜው ነው፤ ሳኦልን ከድቶ ወደ እኔ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ሊያሳዝነኝ የሚችል ምንም ዐይነት በደል ሠርቶ አልተገኘም” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፍልስጥኤማውያንም አለቆች፦ እነዚህ ዕብራውያን በዚህ ምን ያደርጋሉ? አሉ፥ አንኩስም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች፦ ይህ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል ባሪያ ዳዊት አይደለምን? እርሱም በእነዚህ ቀኖች በእነዚህ ዓመታት ከእኔ ጋር ነበረ፥ ወደ እኔም ከተጠጋበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ምንም አላገኘሁበትም አላቸው። |
ከአመለጡትም አንድ ሰው መጣ፤ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፤ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊው የመምሬ ዛፍ ይኖር ነበር፤ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።
ዳዊትም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሳኦልን ሊወጋ በመጣ ጊዜ ከምናሴ ወገን ሰዎች ወደ ዳዊት ከዱ፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን፥ “በራሳችን ላይ ጉዳት አድርጎ ወደ ጌታው ወደ ሳኦል ይመለሳል” ሲሉ ተማክረው ሰድደውታልና እርሱ አልረዳቸውም።
ዳዊትም ወደ ሴቄላቅ ሲሄድ ከምናሴ ወገን የምናሴ ሻለቆች የነበሩ ዓድና፥ ዮዛባት፥ ይዲኤል፥ ሚካኤል፥ ዮዛባት፥ ኤሊሁና ጼልታይ ወደ እርሱ ከዱ።
ሊቃነ ካህናትና ሎሌዎቻቸውም ባዩት ጊዜ፥ “ስቀለው! ስቀለው!” እያሉ ጮሁ፤ ጲላጦስም፥ “እናንተ ራሳችሁ ውሰዱና ስቀሉት፤ እኔስ በእርሱ ላይ በደል አላገኘሁበትም” አላቸው።
ሁለታቸውም ወደ ፍልስጥኤማውያን ሰፈር ገቡ፤ ፍልስጥኤማውያንም “እነሆ፥ ዕብራውያን ከተሸሸጉበት ጕድጓድ ይወጣሉ” አሉ።
እግዚአብሔር ለጌታዬ የታመነ ቤትን ይሠራለታልና፥ የጌታዬንም ጦርነት እግዚአብሔር ይዋጋለታልና የእኔን የባሪያህን ኀጢኣት፥ እባክህ፥ ይቅር በል፤ በዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህም።
ዳዊትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳኦል እጅ እሞታለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ከመሸሸ በቀር የሚሻለኝ የለም፤ ሳኦልም በእስራኤል አውራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተዋል፤ እንዲሁም ከእጁ እድናለሁ” አለ።
አንኩስም ዳዊትን ጠርቶ፥ “ሕያው እግዚአብሔርን! አንተ በፊቴ ጻድቅና ደግ ነህ፤ ከእኔም ጋር በጭፍራው በኩል መውጣትህና መግባትህ በፊቴ መልካም ነው፤ ወደ እኔ ከመጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አንዳች ክፋት አላገኘሁብህም፤ ነገር ግን በአለቆች ዘንድ አልተወደድህም።
ፍልስጥኤማውያንም የእልልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ “በዕብራውያን ሰፈር ያለው ይህ ታላቅ የእልልታ ድምፅ ምንድን ነው?” አሉ። የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደ ደረሰች አስተዋሉ።