የእስራኤልም ንጉሥ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፥ “ልብሴን ለውጬ ወደ ሰልፍ እገባለሁ፤ አንተ ግን የእኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ ልብሱን ለውጦ ወደ ሰልፍ ገባ።
1 ሳሙኤል 28:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም መልኩን ለውጦ፥ ሌላ ልብስም ለብሶ ሄደ፤ ሁለትም ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ በሌሊትም ወደ ሴቲቱ መጡ። ሳኦልም፥ “እባክሽ በመናፍስት አምዋርቺልኝ፤ የምልሽንም አስነሽልኝ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሳኦል ሌላ ልብስ በመልበስ መልኩን ለውጦ ከሁለት ሰዎች ጋራ በሌሊት ወደ ሴቲቱ ሄደ። እርሱም፣ “እባክሽ፣ ጠንቍዪልኝ፤ የምነግርሽንም ሰው አስነሺልኝ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሳኦል ሌላ ልብስ በመልበስ መልኩን ለውጦ ከሁለት ሰዎች ጋር በሌሊት ወደ ሴቲቱ ሄደ። እርሱም፥ “እባክሽ፥ መናፍስትን ጠይቂልኝ፤ የምነግርሽንም ሰው አስነሺልኝ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም ልብሱን ለውጦ ማንነቱ እንዳይታወቅ በማድረግ በሌሊት ሁለት ሰዎች አስከትሎ ሴትዮዋን ለማየት ሄደ፤ እዚያም እንደ ደረሰ “መናፍስትን ጠይቀሽ ወደ ፊት ስለሚሆነው ነገር አስረጂኝ፤ ስሙንም የምጠራልሽን ሰው አስነሽልኝ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም መልኩን ለውጦ ሌላ ልብስም ለብሶ ሄደ፥ ሁለትም ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፥ በሌሊትም ወደ ሴቲቱ መጡ። እርሱም፦ እባክሽ፥ በመናፍስት አምዋርቺልኝ፥ የምልሽንም አስነሽልኝ አላት። |
የእስራኤልም ንጉሥ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፥ “ልብሴን ለውጬ ወደ ሰልፍ እገባለሁ፤ አንተ ግን የእኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ ልብሱን ለውጦ ወደ ሰልፍ ገባ።
አንድ ሰውም ቀስቱን ድንገት ገትሮ የእስራኤልን ንጉሥ በሳንባውና በደረቱ መካከል ወጋው፤ ሰረገለኛውንም፥ “መልሰህ ንዳ፤ ተወግቻለሁና ከሰልፍ ውስጥ አውጣኝ” አለው።
እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኀጢአት፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪን ጠየቀ።
የእስራኤል ንጉሥም ኢዮሣፍጥን፥ “ልብሴን ለውጬ ወደ ጦርነት እገባለሁ፤ አንተ ግን የእኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ ልብሱን ለወጠ፤ ወደ ሰልፍም ገባ።
ኢዮስያስ ግን ይዋጋው ዘንድ ተጽናና እንጂ ፊቱን ከእርሱ አልመለሰም፤ በእግዚአብሔርም አፍ የተነገረውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፤ በመጊዶንም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።
እነርሱም፥ “ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ” ባሉአችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?
ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር።
ለእስራኤልም ቤት ምልክት አድርጌሃለሁና በፊታቸው ዕቃህን በትከሻህ ላይ አንግተው፤ በጨለማም ተሸክመህ ውጣ፤ ምድሪቱንም እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።”