La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 28:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳሙ​ኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አል​ቅ​ሰ​ው​ለት ነበር፤ በከ​ተ​ማ​ውም በአ​ር​ማ​ቴም ቀብ​ረ​ውት ነበር። ሳኦ​ልም መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ከም​ድር አጥ​ፍቶ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም ሁሉ በገዛ ከተማው በአርማቴም አልቅሰው ቀበሩት። ሳኦል ሙታን ሳቢዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን ከምድሪቱ አባርሯቸው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም ሁሉ በገዛ ከተማው በራማ አልቅሰው ቀበሩት። ሳኦልም ሙታን ሳቢዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን ከምድሪቱ አባሯቸው ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነሆ፥ ሳሙኤል ከሞተ ቈየት ብሎአል፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ለእርሱ በማዘን አልቅሰው በሚኖርባት በራማ ቀብረውታል፤ ቀደም ሲል ሳኦል ጠንቋዮችንና ሙታን ጠሪዎችን ከእስራኤል ምድር እንዲባረሩ አስገድዶአቸው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳሙኤል ግን ሞቶ ነበር፥ እስራኤልም ሁሉ አልቅሰውለት ነበር፥ በከተማውም በአርማቴም ቀብረውት ነበር። ሳኦልም መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር አጥፍቶ ነበር።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 28:3
12 Referencias Cruzadas  

አባ​ቷም እር​ስ​ዋን እን​ዳ​ይ​ሰ​ጠው ፈጽሞ እንቢ ቢል እንደ ደና​ግል ማጫ ያህል ማጫ​ዋን ይስ​ጠው።


“ከመ​ተ​ተኛ ጋር አንድ አት​ሁኑ።


“ወደ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ችና ወደ ጠን​ቋ​ዮች አት​ሂዱ፤ እን​ዳ​ት​ረ​ክ​ሱ​ባ​ቸ​ውም አት​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸው፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


“ወንድ ወይም ሴት መና​ፍ​ስ​ትን ቢጠሩ፥ ወይም ጠን​ቋ​ዮች ቢሆኑ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በድ​ን​ጋ​ይም ይው​ገ​ሩ​አ​ቸው፤ በደ​ለ​ኞች ናቸ​ውና።”


“እነ​ር​ሱን ተከ​ትሎ ያመ​ነ​ዝር ዘንድ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን የሚ​ከ​ተል ሰው ቢኖር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ዳ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


ኀጢ​ኣት እንደ ምዋ​ር​ተ​ኝ​ነት ናትና አም​ል​ኮተ ጣዖ​ትም ደዌ​ንና ኀዘ​ንን ያመ​ጣል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ንቀ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ እን​ዳ​ት​ሆን ናቀህ” አለው።


ሳሙ​ኤ​ልም ሞተ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ በአ​ር​ማ​ቴ​ምም በቤቱ ቀበ​ሩት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ወረደ።


ሴቲ​ቱም፥ “እነሆ፥ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ከም​ድር እን​ዳ​ጠፋ ሳኦል ያደ​ረ​ገ​ውን ታው​ቃ​ለህ፤ ስለ​ምን እኔን ለማ​ስ​ገ​ደል ለነ​ፍሴ ወጥ​መድ ታደ​ር​ጋ​ለህ?” አለ​ችው።


ቤቱም በዚያ ነበ​ረና ወደ አር​ማ​ቴም ይመ​ለስ ነበር፤ በዚ​ያም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ።