እነርሱም፥ “ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ” ባሉአችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?
1 ሳሙኤል 28:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም፥ “ማንን ላስነሣልህ?” አለችው፤ እርሱም፥ “ሳሙኤልን አስነሽልኝ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋም፣ “ማንን ላስነሣልህ?” ብላ ጠየቀችው። እርሱም፣ “ሳሙኤልን አስነሺልኝ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴትዮዋም፥ “ማንን ላስነሣልህ?” ብላ ጠየቀችው። እርሱም፥ “ሳሙኤልን አስነሺልኝ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ታዲያ ማንን ላስነሣልህ?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም “ሳሙኤልን አስነሽልኝ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም፦ ማንን ላስነሣልህ? አለች፥ እርሱም፦ ሳሙኤልን አስነሽልኝ አለ። |
እነርሱም፥ “ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ” ባሉአችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?
በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም፥ በወፍም የሚያሟርት በአንተ ዘንድ አይገኝ።
ሴቲቱም ሳሙኤልን ባየች ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኸች፤ ሴቲቱም ሳኦልን፥ “አንተ ሳኦል ስትሆን ለምን አታለልኸኝ?” ብላ ተናገረችው።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ለምን አወክኸኝ? ለምንስ አስነሣኸኝ?” አለው። ሳኦልም መልሶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ይወጉኛልና እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቆአል፤ በነቢያት ወይም በሕልም አላሚዎች አልመለሰልኝም፤ ስለዚህም የማደርገውን ታስታውቀኝ ዘንድ ጠራሁህ” አለው።