ከዚያም በኋላ ዳዊት፥ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “ውጣ” አለው። ዳዊትም፥ “ወዴት ልውጣ?” አለ። እርሱም፥ “ወደ ኬብሮን ውጣ” አለው።
1 ሳሙኤል 23:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም፥ “ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያንን ልምታን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “ሂድ፤ ፍልስጥኤማውያንን ምታ፤ ቂአላንም አድን” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “እነዚህን ፍልስጥኤማውያን ሄጄ ልምታን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “ሂድ፤ ፍልስጥኤማውያንን ምታ፤ ቅዒላንም አድናት” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “እነዚህን ፍልስኤማውያን ሄጄ ልምታን?” ሲል ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “ሂድ፤ ፍልስጥኤማውያንን ምታ፤ ቅዒላንም አድናት” ብሎ መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊት “ሄጄ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ልጣልባቸውን?” ሲል የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ! በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ በመጣል ቀዒላን ከጥፋት አድን” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም፦ ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያን ልምታን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ሂድ፥ ፍልስጥኤማውያንን ምታ ቅዒላንም አድን አለው። |
ከዚያም በኋላ ዳዊት፥ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “ውጣ” አለው። ዳዊትም፥ “ወዴት ልውጣ?” አለ። እርሱም፥ “ወደ ኬብሮን ውጣ” አለው።
ዳዊትም፥ “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፥ “ፍልስጥኤማውያንን በርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ” አለው።
ዳዊትም እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “በኋላቸው ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ አትውጣ።
ዳዊትም፥ “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ” አለው።
በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃሉም ይግቡ።”
እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች፥ “ከነዓናውያንን የሚወጋልን ማን አለቃ ይወጣልናል?” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጠየቁ።
ሳሙኤልም፦ ያ ሰው እዚህ ይመጣ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “እነሆ፥ በዕቃ መካከል ተሸሽጎአል” ብሎ መለሰ።
ሳኦልም፥ “ልውረድና ፍልስጥኤማውያንን ልከተልን? በእስራኤልስ እጅ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀው። በዚያ ቀን ግን እግዚአብሔር አልመለሰለትም።
የዳዊትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ በዚህ በይሁዳ መቀመጥ እንፈራለን፤ ይልቁንስ ፍልስጥኤማውያንን ለመዝረፍ ወደ ቂአላ ብንሄድ እንዴት እንሆናለን?” አሉት።
ዳዊትም ደግሞ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም መልሶ፥ “ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁና ተነሥተህ ወደ ቂአላ ውረድ” አለው።
ዳዊትም፥ “የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እርሱም፥ “ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮኞቹን ታድናለህና ፍለጋቸውን ተከተል” ብሎ መለሰለት።