Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 23:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጅ አብ​ያ​ታር ወደ ዳዊት ወደ ቂአላ በኰ​በ​ለለ ጊዜ ኤፉ​ዱን ይዞ ወርዶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ወደ ቅዒላ ወደ ዳዊት በሸሸ ጊዜ፣ ኤፉዱን ይዞ ወርዶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ወደ ቅዒላ ወደ ዳዊት በሸሸ ጊዜ፥ ኤፉዱን ይዞ ወርዶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የአቤሜሌክ ልጅ አብያታር አምልጦ በቀዒላ ከዳዊት ጋር በተባበረ ጊዜ ወደዚያ የመጣው ኤፉዱን እንደ ያዘ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እንዲህም ሆነ፥ የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ወደ ዳዊት ወደ ቅዒላ በኮበለለ ጊዜ ኤፉዱን ይዞ ወርዶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 23:6
12 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበ​ርህ፤ ነገር ግን የአ​ም​ላ​ክን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፊት ስለ ተሸ​ከ​ምህ፥ አባ​ቴም የተ​ቀ​በ​ለ​ውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀ​በ​ልህ አል​ገ​ድ​ል​ህ​ምና በዓ​ና​ቶት ወዳ​ለው ወደ እር​ሻህ ፈጥ​ነህ ሂድ” አለው።


“ልብሰ መት​ከ​ፉ​ንም ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከተ​ፈ​ተለ ከቀይ ግምጃ በግ​ብረ መርፌ የተ​ሠራ፥ የተ​ለየ የሽ​መና ሥራ ያድ​ርጉ።


በዚ​ያም ቀን አኪያ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ይለ​ብስ ነበ​ርና ሳኦል፥ “ኤፉ​ድን አምጣ” አለው።


የዔሊ ልጅ፥ የፊ​ን​ሐስ ልጅ፥ የዮ​ካ​ብድ ወን​ድም፥ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ በሴሎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህን የሆነ፥ ኤፉ​ድም የለ​በሰ አኪያ አብሮ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ዮና​ታን እንደ ሄደ አላ​ወ​ቁም ነበር።


ከአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጆች ስሙ አብ​ያ​ታር የሚ​ባል አንዱ ልጅ አም​ልጦ ሸሸ፤ ዳዊ​ት​ንም ተከ​ተለ።


ዳዊ​ትም፥ “ልሂ​ድን? እነ​ዚ​ህ​ንስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ልም​ታን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሂድ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ምታ፤ ቂአ​ላ​ንም አድን” አለው።


ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወደ ቂአላ ሄዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ተዋጉ፤ እነ​ር​ሱም ከፊቱ ሸሹ፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ማረኩ፤ በታ​ላ​ቅም አገ​ዳ​ደል ገደ​ሉ​አ​ቸው። ዳዊ​ትም በቂ​አላ የሚ​ኖ​ሩ​ትን አዳነ።


ለሳ​ኦ​ልም ዳዊት ወደ ቂአላ እንደ መጣ ተነ​ገ​ረው፤ ሳኦ​ልም፥ “መዝ​ጊ​ያና መወ​ር​ወ​ሪያ ወዳ​ለ​ባት ከተማ ገብቶ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል” አለ።


ዳዊ​ትም ሳኦል በእ​ርሱ ለክ​ፋት ዝም እን​ደ​ማ​ይል ዐወቀ፤ ዳዊ​ትም ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኤፉድ ወደ​ዚህ አምጣ” አለው።


ዳዊ​ትም የአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክን ልጅ ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “ኤፉ​ዱን አቅ​ር​ብ​ልኝ” አለው፤ አብ​ያ​ታ​ርም ኤፉ​ዱን ለዳ​ዊት አቀ​ረ​በ​ለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos