አብርሃምም በዐዘቅተ መሐላ አጠገብ የተምር ዛፍን ተከለ፤ በዚያም የዘለዓለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ።
1 ሳሙኤል 22:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ያሉበት ቦታ እንደ ታወቀ ሰማ። ሳኦልም በራማ በሚገኘው በመሰማርያው ቦታ በኮረብታው ላይ ተቀምጦ በእጁም ጦር ይዞ ነበር፤ ብላቴኖቹም ሁሉ በአጠገቡ ቆመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ ዳዊትና ከርሱ ጋራ የነበሩ ሰዎች መገኘታቸውን በሰማ ጊዜ፣ በጊብዓ ኰረብታ ላይ በአጣጥ ዛፍ ሥር፣ ጦሩን በእጁ ይዞ ተቀምጦ ነበር፤ ሹማምቱም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፥ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች መገኘታቸውን በሰማ ጊዜ፥ በጊብዓ ኰረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ የሚጠራ ዛፍ ሥር፥ ጦሩን በእጁ ይዞ ተቀምጦ ነበር፤ አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዕለታት አንድ ቀን ሳኦል ጦሩን በእጁ እንደ ያዘ በጊብዓ በሚገኝ ኮረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ በሚጠራ ዛፍ ሥር ተቀምጦ ነበር፤ ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም በዙሪያው ቆመው ነበር፤ በዚህን ጊዜ ዳዊትና ተከታዮቹ በአንድ ስፍራ መኖራቸው ለሳኦል ተነገረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንደ ተገለጡ ሰማ። ሳኦልም በጊብዓ በአጣጥ ዛፍ በታች በኮረብታው ላይ ተቀምጦ በእጁም ጦር ይዞ ነበር፥ ባሪያዎቹም ሁሉ በአጠገቡ ቆመው ነበር። |
አብርሃምም በዐዘቅተ መሐላ አጠገብ የተምር ዛፍን ተከለ፤ በዚያም የዘለዓለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ።
እርስዋም በኤፍሬም ተራራ በቤቴልና በኢያማ መካከል “የዲቦራ ዘንባባ” ተብሎ በሚጠራው ዛፍ ሥር ተቀምጣ ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እርስዋ ለፍርድ ይወጡ ነበር።
ሳኦልም በመጌዶን ባለው በሮማኑ ዛፍ በታች በኮረብታው ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ስድስት መቶ የሚያህል ሰው ነበረ።
እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤቱም ውስጥ ትንቢት ተናገረ። ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።
ሳኦልም ሊገድለው በዮናታን ላይ ጦሩን አነሣ፤ ዮናታንም አባቱ ዳዊትን ይገድለው ዘንድ ያች ክፉ ነገር እንደ ተቈረጠች ዐወቀ።