1 ሳሙኤል 22:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢዩ ጋድም ዳዊትን፥ “ተነሥተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ እንጂ በአንባው ውስጥ አትቀመጥ” አለው፤ ዳዊትም ሄደ፤ ወደ ሳሬቅ ከተማም መጥቶ ተቀመጠ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፣ “በዐምባው ውስጥ አትቈይ፤ ሂድና ወደ ይሁዳ ምድር ግባ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁን እንጂ ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፥ “በዐምባው ውስጥ አትቆይ፤ ሂድና ወደ ይሁዳ ምድር ግባ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ነቢዩ ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ “በዚህ አትቈይ፤ አሁኑኑ ፈጥነህ ወደ ይሁዳ ሂድ” ሲል ነገረው፤ ስለዚህም ዳዊት ከዚያ ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነቢዩ ጋድም ዳዊትን፦ ተነሥተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ እንጂ በአምባው ውስጥ አትቀመጥ አለው፥ ዳዊትም ተነሥቶ ወደ ሔሬት ዱር መጣ። |
የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።
ይህንም ትእዛዝ እግዚአብሔር በነቢያቱ እጅ አዝዞአልና እንደ ዳዊትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢዩም እንደ ናታን ትእዛዝ፥ ጸናጽልና በገና፥ መሰንቆም አስይዞ ሌዋውያንን በእግዚአብሔር ፊት አቆመ።