ዳዊትም፥ “ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሃለሁና አትፍራ፤ የአባትህን አባት የሳኦልን መሬት ሁሉ እመልስልሃለሁ፤ አንተም ሁል ጊዜ ከገበታዬ እንጀራን ትበላለህ” አለው።
1 ሳሙኤል 22:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ወዲህ ከእኔ ጋር ተቀመጥ፤ አትፍራ፤ ለእኔ ነፍስ የደኅንነት ቦታን እንደምፈልግ ለአንተም ነፍስ የደኅንነት ቦታን እፈልጋለሁና፥ ከእኔም ጋር ተጠብቀህ ትኖራለህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ከእኔ ጋራ ቈይ፤ አትፍራ፤ የአንተን ሕይወት የሚፈልግ የእኔን ሕይወት የሚፈልግ ነውና። ዐብረኸኝ በሰላም ትኖራለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ከእኔ ጋር ቆይ፤ አትፍራ፤ የአንተን ሕይወት የሚፈልግ የእኔን ሕይወት ይፈልጋል። አብረኸኝ በሰላም ትኖራለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ግን ከእኔ ጋር ኑር፤ አይዞህ አትፍራ፤ በእርግጥ ሳኦል አንተንም እኔንም ለመግደል ይፈልጋል፤ ነገር ግን አንተ ከእኔ ጋር በሰላም ትኖራለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሴን የሚፈልግ የአንተን ነፍስ ይፈልጋልና፥ ከእኔም ጋር ተጠብቀህ ትኖራለህና በእኔ ዘንድ ተቀመጥ፥ አትፍራ አለው። |
ዳዊትም፥ “ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሃለሁና አትፍራ፤ የአባትህን አባት የሳኦልን መሬት ሁሉ እመልስልሃለሁ፤ አንተም ሁል ጊዜ ከገበታዬ እንጀራን ትበላለህ” አለው።
ሴራውም ከሶርህያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ነበረ፤ እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ይረዱት ነበር።
ንጉሡም ካህኑን አብያታርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፥ አባቴም የተቀበለውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀበልህ አልገድልህምና በዓናቶት ወዳለው ወደ እርሻህ ፈጥነህ ሂድ” አለው።
እኔ፦ ከጌታው የሚበልጥ አገልጋይ የለም ያልኋችሁን ቃሌን ዐስቡ፤ እኔን ካሳደዱ እናንተንም ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው ቢሆንስ ቃላችሁንም በጠበቁ ነበር።
እኔ በዓለም ከእነርሱ ጋር ሳለሁ ግን የሰጠኸኝን በስምህ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም፤ የመጽሐፉም ቃል ይፈጸም ዘንድ ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ አንድ ስንኳን አልጠፋም።
ለእርሱም “የአባቴ የሳኦል እጅ አታገኝህምና አትፍራ፤ አንተም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆናለህ፤ እኔም ከአንተ በታች እሆናለሁ፤ ይህን ደግሞ አባቴ ሳኦል ያውቃል” አለው።