በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃሉም ይግቡ።”
1 ሳሙኤል 22:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርንም ጠየቀለት፤ ስንቅንም ሰጠው፤ የፍልስጥኤማዊውንም የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢሜሌክም እግዚአብሔርን ጠየቀለት፤ እንዲሁም ስንቅና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ምን ማድረግ እንደሚገባው አቢሜሌክ ጌታን ጠይቆለታል፤ ለዳዊትም ጥቂት ምግብና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጥቶታል” ሲል ተናገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ምን ማድረግ እንደሚገባው አቤሜሌክ እግዚአብሔርን ጠይቆለታል፤ ከዚያም በኋላ ለዳዊት ጥቂት ምግብና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጥቶታል” ሲል ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርንም ጠየቀለት፥ ስንቅንም ሰጠው፥ የፍልስጥኤማዊውንም የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው አለው። |
በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃሉም ይግቡ።”
ሳሙኤልም፦ ያ ሰው እዚህ ይመጣ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “እነሆ፥ በዕቃ መካከል ተሸሽጎአል” ብሎ መለሰ።
ንጉሡም የአኪጦብን ልጅ ካህኑን አቤሜሌክን፥ በኖብም ያሉትን ካህናት፥ የአባቱን ልጆች ሁሉ ልኮ አስጠራቸው፤ ሁላቸውም ወደ ንጉሡ መጡ።
ሳኦልም፥ “አንተ ከእሴይ ልጅ ጋር ለምን ዶለትህብኝ? እንጀራና ሰይፍ ሰጠኸው፤ ዛሬም እንደ ተደረገው ጠላት ሆኖ ይነሣብኝ ዘንድ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ ጠየቅህለት” አለው።
በውኑ ስለ እርሱ እግዚአብሔርን እጠይቅ ዘንድ ዛሬ ጀመርሁን? ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ ባሪያህ ይህን ሁሉ ትልቅ ወይም ጥቂት ቢሆን አላውቅምና ንጉሡ እንደዚህ ያለውን ነገር በእኔ በባሪያውና በአባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያኑር” አለ።
ዳዊትም፥ “የቂአላ ሰዎች እኔንና ሰዎቼን በሳኦል እጅ አሳልፈው ይሰጡናልን?” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አሳልፈው ይሰጡአችኋል” ብሎ ተናገረ።
ዳዊትም፥ “ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያንን ልምታን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “ሂድ፤ ፍልስጥኤማውያንን ምታ፤ ቂአላንም አድን” አለው።
ዳዊትም ደግሞ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም መልሶ፥ “ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁና ተነሥተህ ወደ ቂአላ ውረድ” አለው።
ዳዊትም፥ “የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እርሱም፥ “ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮኞቹን ታድናለህና ፍለጋቸውን ተከተል” ብሎ መለሰለት።