1 ሳሙኤል 21:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአንኩስ ብላቴኖችም፥ “ይህ ዳዊት የሀገሩ ንጉሥ አይደለምን? ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም ዐሥር ሺህ ገደለ ብለው ሴቶች በዘፈን የዘመሩለት እርሱ አይደለምን?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአንኩስ አገልጋዮችም፣ “የምድሪቱ ንጉሥ ዳዊት ይህ አይደለምን? ደግሞስ፣ “ ‘ሳኦል ሺሕ ገደለ፤ ዳዊት ግን ዐሥር ሺሕ ገደለ’ ብለው በጭፈራቸው የዘፈኑለትስ እርሱ አይደለምን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአኪሽ አገልጋዮችም፥ “የምድሪቱ ንጉሥ ዳዊት ይህ አይደለምን? ደግሞስ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ፤ ዳዊት ዐሥር ሺህ ገደለ’ ብለው በጭፈራቸው የዘፈኑለትስ እርሱ አይደለምን?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሡ ባለሟሎች የሆኑት ባለሥልጣኖች “ይህ በአገሩ የነገሠው ዳዊት አይደለምን? ‘ሳኦል ሺህ ገዳይ! ዳዊት ዐሥር ሺህ ገዳይ!’ እያሉ ሴቶች በጭፍራ የዘፈኑለት እርሱ አይደለምን?” ሲሉ አኪሽን ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአንኩስ ባሪያዎችም፦ ይህ ዳዊት የአገሩ ንጉሥ አይደለምን? ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም እልፍ ገደለ ብለው ሴቶች በዘፈን የዘመሩለት እርሱ አይደለምን? አሉት። |
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? የዘይቱን ቀንድ ሞልተህ ና፤ በልጆቹ መካከል ለእኔ ንጉሥ አዘጋጅቼአለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ” አለው።
ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፤ ወደ አርማቴምም ወደ ሳሙኤል መጣ፤ ሳኦልም ያደረገበትን ሁሉ ነገረው፤ እርሱና ሳሙኤልም ሄዱ፤ በአውቴዘራማም ተቀመጡ።
ዳዊትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳኦል እጅ እሞታለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ከመሸሸ በቀር የሚሻለኝ የለም፤ ሳኦልም በእስራኤል አውራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተዋል፤ እንዲሁም ከእጁ እድናለሁ” አለ።