1 ሳሙኤል 20:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፥ “አንድ ነገር ሆኖ ይሆናል፤ ምንአልባትም ንጹሕ አይደለም ይሆናል፤ በእውነትም ንጹሕ አይደለም” ብሎ አስቦአልና በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ “ዳዊት በሥርዐቱ መሠረት እንዳይነጻ የሚያደርገው አንድ ነገር ገጥሞታል፤ በርግጥም አልነጻም” ብሎ ስላሰበ፣ በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፥ “ዳዊት በሥርዓቱ መሠረት እንዳይነጻ የሚያደርገው አንድ ነገር ገጥሞታል፤ በእርግጥም አልነጻም” ብሎ ስላሰበ፥ በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ሳኦል በዚያን ቀን ምንም ቃል አልተናገረም፤ ሳኦል ስለ ዳዊት ሲያስብ “ምናልባት አንድ ነገር ገጥሞት ይሆናል፤ ወይም በሕጉ መሠረት በሥርዓት አልነጻም ይሆናል” በማለት ያሰላስል ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ አንድ ነገር ሆኖአል፥ ንጹሕም አይደለም፥ በእውነት ንጹሕ አይደለም ብሎ አስቦአልና በዚያን ቀን ምንም አልተናገረም። |
በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ ሁሉ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ የእርሱን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።
ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩሳን የሚሆኑ እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም በድናቸውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።
ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ በድኑንም የሚያነሣ፤ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።
እርሱም፥ “ለሰላም ነው፤ ለእግዚአብሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ፤ ቅዱሳን ሁኑ፤ ከእኔም ጋር ዛሬ ደስ ይበላችሁ፤ ከእኔም ጋር ወደ መሥዋዕቱ ኑ” አለ። እሴይንና ልጆቹንም ቀደሳቸው፤ ወደ መሥዋዕቱም ጠራቸው።
ከመባቻም በኋላ በማግሥቱ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶውን ነበረ፤ ሳኦልም ልጁን ዮናታንን፥ “የእሴይ ልጅ ትናትና ዛሬ ወደ ግብር ያልመጣ ስለምን ነው?” አለው።