እነሆም፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በእግዚአብሔር ቃል ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤ ኢዮርብዓምም መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር።
1 ሳሙኤል 2:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በግብፅ በፈርዖን ቤት ባሪያዎች ሳሉ ለአባትህ ቤት ተገለጥሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የአባትህ ቤት በግብጽ ምድር በፈርዖን እጅ በነበረ ጊዜ ራሴን ገለጥሁለት? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ እግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘በግብጽ በፈርዖን ቤት ባርያ ሳሉ ለአባትህ ቤት ተገለጥሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእግዚአብሔር የተላከ አንድ ነቢይ ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በፈርዖን ቤት ባሪያዎች በነበሩ ጊዜ ለቀድሞ አባትህ ለአሮን ራሴን ገለጥሁለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ አለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ በግብጽ በፈርዖን ቤት ባሪያ ሳለ ለአባትህ ቤት ተገለጥሁ፥ |
እነሆም፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በእግዚአብሔር ቃል ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤ ኢዮርብዓምም መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር።
በሴሎም በዔሊ ቤት ላይ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ ሰሎሞን አብያታርን ከእግዚአብሔር ክህነት አወጣው።
እግዚአብሔርም አሮንን አለው፥ “ሄደህ በምድረ በዳ ሙሴን ተገናኘው፤” ሄዶም በእግዚአብሔር ተራራ ተገናኘው፤ እርስ በርሳቸውም ተሳሳሙ።
ሴቲቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፤ ከወዴትም እንደ መጣ ጠየቅሁት፥ እርሱም ስሙን አልነገረኝም።
እግዚአብሔር ወደ እስራኤል ልጆች ነቢይ ላከ፤ እርሱም አለ፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፤ ከባርነትም ቤት አስለቀቅኋችሁ፤
ወደ ተራራማውም ወደ ኤፍሬም ሀገር ሄዱ፤ በሲልካ ምድርም አለፉ፤ አላገኙአቸውምም፤ በፋስቂም ምድር አለፉ፤ በዚያም አልነበሩም፤ በኢያሚንም ምድር አለፉ፤ አላገኙአቸውምም።
ብላቴናውም፥ “እነሆ፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በዚህች ከተማ አለ፤ እርሱም የተከበረ ሰው ነው፤ የሚናገረው ሁሉ በእውነት ይፈጸማል፤ አሁንም ወደዚያ እንሂድ፤ ምናልባት የምንሄድበትን መንገድ ይነግረናልና” አለው።