1 ሳሙኤል 19:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አውቴዘራማም ሄደ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ደግሞ ወረደ፤ እርሱም ሄደ፤ ወደ አውቴዘራማም እስኪመጣ ድረስ ትንቢት ይናገር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሳኦል በአርማቴም ወደምትገኘው ወደ ነዋት ዘራማ ሄደ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በርሱም ላይ ደግሞ ወረደ፤ ወደ ነዋት እስኪደርስ ድረስም ትንቢት እየተናገረ ተጓዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሳኦል በራማ ወደምትገኘው ወደ የራማዋ ናዮት ሄደ፤ ሲሄድ ሳለም የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ ደግሞ ወረደ፤ ወደ ናዮት እስኪደርስ ድረስም ትንቢት እየተናገረ ተጓዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደዚያም በማምራት ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ ወረደበት፤ እስከ ናዮት በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ትንቢት ይናገር ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አርማቴምም አገር ወደ ነዋትዘራማ ሄደ፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ደግሞ ወረደ፥ እርሱም ሄደ፥ ወደ አርማቴምም አገር ወደ ነዋትዘራማ እስኪመጣ ድረስ ትንቢት ይናገር ነበር። |
በዚያ ቀን ብዙዎች ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል።
ይህንም ከልቡ የተናገረው አይደለም፤ ነገር ግን በዚያች ዓመት የካህናት አለቃ ነበርና ጌታችን ኢየሱስ ስለ ሕዝብ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ይሞት ዘንድ ስላለው ይህን ትንቢት ተናገረ።
ትንቢት ብናገር፥ የተሰውረውን ሁሉ፥ ጥበብንም ሁሉ ባውቅ፥ ተራራ እስከ ማፍለስ የሚያደርስ ፍጹም እምነትም ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
ወደዚያም ኮረብታ በደረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነቢያት ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ ወረደ፤ በመካከላቸውም ትንቢት ተናገረ።
ከዚያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው፥ “አባቱስ ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለዚህም “ሳኦል ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌ ሆነ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በአንተ ይወርዳል፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፤ እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትለወጣለህ።
እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤቱም ውስጥ ትንቢት ተናገረ። ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።
ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፤ ወደ አርማቴምም ወደ ሳሙኤል መጣ፤ ሳኦልም ያደረገበትን ሁሉ ነገረው፤ እርሱና ሳሙኤልም ሄዱ፤ በአውቴዘራማም ተቀመጡ።
ሳኦልም ዳዊትን ያመጡት ዘንድ መልእክተኞችን ላከ፤ የነቢያትንም ጉባኤ አገኙ፤ ሳሙኤልም አለቃቸው ሆኖ በመካከላቸው ቆሞ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በሳኦል መልእክተኞች ላይ ወረደ፤ እነርሱም ትንቢት ይናገሩ ጀመር።
ሳኦልም እጅግ ተቈጣ፤ እርሱም ደግሞ ወደ አርማቴም መጣ፤ በመሴፋም አውድማ ወዳለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድጓድ ደረሰ። “ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው?” ብሎ ጠየቀ፤ “እነሆ፥ በአውቴዘራማ ናቸው” አሉት።