1 ሳሙኤል 19:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ዳዊትን ከግንብ ጋር ያጣብቀው ዘንድ ጦሩን ወረወረ፤ ዳዊትም ከሳኦል ፊት ዘወር አለ፤ ጦሩም በግንቡ ውስጥ ተተከለ፤ በዚያም ሌሊት ዳዊት ሸሸቶ አመለጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም ከግድግዳው ጋራ ሊያጣብቀው ጦሩን ወረወረበት፤ ነገር ግን ዳዊት ዘወር በማለቱ ሳኦል የወረወረው ጦር በግድግዳው ላይ ተሰካ። በዚያች ሌሊት ዳዊት ሸሽቶ አመለጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም ከግድግዳው ጋር ሊያጣብቀው ጦሩን ወረወረበት፤ ነገር ግን ዳዊት ዘወር በማለቱ ሳኦል የወረወረው ጦር እግድግዳው ላይ ተሰካ። በዚያች ሌሊት ዳዊት ሸሽቶ አመለጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል ዳዊትን ወግቶ ከግድግዳው ጋር ሊያጣብቀው በማሰብ ጦሩን ወረወረበት፤ ዳዊት ግን ዞር በማለቱ ጦሩ በግድግዳ ላይ ተተከለ፤ ዳዊትም ከዚያ ሸሽቶ አመለጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ዳዊትን ከግንብ ጋር ያጣብቀው ዘንድ ጦሩን ወረወረ፥ ዳዊትም ከሳኦል ፊት ዘወር አለ፥ ጦሩም በግንቡ ውስጥ ተተከለ፥ በዚያም ሌሊት ዳዊት ሸሽቶ አመለጠ። |
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ እንዲከናወን አላደርግም፤ በአንቺ ላይ ለፍርድ የሚነሣውን ድምፅ ሁሉ ታጠፊያለሽ፤ ጠላቶችሽም ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ እግዚአብሔርንም ለሚያገለግሉ ርስት አላቸው፤ ጻድቃኔም ትሆኑኛላችሁ ይላል እግዚአብሔር።
“ምሕረታችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ጠል ነውና ኤፍሬም ሆይ! ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድርግልህ?
በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
የእሳት ኀይልን አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው በረቱ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ።
እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤቱም ውስጥ ትንቢት ተናገረ። ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።
ሳኦልም ሊገድለው በዮናታን ላይ ጦሩን አነሣ፤ ዮናታንም አባቱ ዳዊትን ይገድለው ዘንድ ያች ክፉ ነገር እንደ ተቈረጠች ዐወቀ።