ከራፋይም ወገን የነበረው ኤስቢ መጣ፤ የጦሩም ሚዛን ክብደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣሪያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊትንም ሊገድለው ፈለገ።
1 ሳሙኤል 17:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጦሩም የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ነበረ፤ የጦሩም ሚዛን ስድስት መቶ ሰቅል ብረት ነበረ፤ ጋሻ ጃግሬውም በፊቱ ይሄድ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጦሩም ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የወፈረ፣ የጦሩም ብረት ስድስት መቶ ሰቅል ያህል የሚመዝን ነበር፤ ጋሻ ጃግሬውም ከፊት ከፊቱ ይሄድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጦሩም ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የወፈረ፥ የጦሩም ብረት ስድስት መቶ ሰቅል ያህል የሚመዝን ነበር፤ ጋሻ ጃግሬውም ከፊት ከፊቱ ይሄድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጦሩ ዘንግ ውፍረቱ የሸማኔ መጠቅለያ ያኽል ነበር፤ የጦሩም ብረት ክብደቱ ሰባት ኪሎ ያኽል ነበር፤ ጋሻውንም ጋሻጃግሬው ተሸክሞለት በፊት በፊቱ ይሄድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጦሩም የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅልያ ነበረ፥ የጦሩም ሚዛን ስድስት መቶ ሰቅል ብረት ነበረ፥ ጋሻ ጃግሬውም በፊቱ ይሄድ ነበር። |
ከራፋይም ወገን የነበረው ኤስቢ መጣ፤ የጦሩም ሚዛን ክብደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣሪያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊትንም ሊገድለው ፈለገ።
ደግሞም በሮም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ የቤተልሔማዊውም የዓሬኦርጌም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው ጎዶልያን ገደለው።
ቁመቱም አምስት ክንድ የነበረውን ረጅሙን ግብፃዊውን ሰው ገደለ፤ በግብፃዊውም እጅ የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር ነበረ፤ እርሱ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፥ ከግብፃዊውም እጅ ጦሩን ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደለው።
ደግሞም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የያዔርም ልጅ ኤልያናን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሜን ገደለ። የጦሩ የቦም እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ሆኖ ተገኘ።