ሙሴም አሮንን፥ “አንድ የወርቅ መሶብ ወስደህ ጎሞር ሙሉ መና አግባበት፤ ለልጅ ልጃችሁም ይጠበቅ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው” አለው።
1 ሳሙኤል 17:54 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም የፍልስጥኤማዊውን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ ጋሻና ጦሩን ግን በድንኳኑ ውስጥ አኖረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም የፍልስጥኤማዊውን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ ነገር ግን የፍልስጥኤማዊውን የጦር መሣሪያዎች በራሱ ድንኳን ውስጥ አስቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም የፍልስጥኤማዊውን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የጦር መሣሪያዎቹን ግን በራሱ ድንኳን ውስጥ አስቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት የጎልያድን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የጎልያድን የጦር መሣሪያዎች ግን በራሱ ድንኳን አስቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም የፍልስጥኤማዊውን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፥ ጋሻ ጦሩን ግን በድንኳኑ ውስጥ አኖረው። |
ሙሴም አሮንን፥ “አንድ የወርቅ መሶብ ወስደህ ጎሞር ሙሉ መና አግባበት፤ ለልጅ ልጃችሁም ይጠበቅ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው” አለው።
ሳኦልም ዳዊትን ፍልስጥኤማዊውን ሊዋጋ ሲወጣ ባየ ጊዜ ለሠራዊቱ አለቃ ለአቤኔር፥ “አቤኔር ሆይ፥ ይህ ብላቴና የማን ልጅ ነው?” አለው። አቤኔርም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ አላውቅም” አለ።
ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ አቤኔር ወሰደው፤ ወደ ሳኦልም ፊት አመጣው፤ የፍልስጥኤማዊውንም ራስ በእጁ ይዞ ነበር።
ካህኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመጐናጸፊያ ተጠቅልላ አለች፤ የምትወስዳት ከሆነ ውሰዳት፤ ከእርስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለምና” አለው። ዳዊትም፥ “ከእርስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እርስዋን ስጠኝ” አለው። እርሱም ሰጠው።