1 ሳሙኤል 17:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው፤ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለ ፤ በዳዊትም እጅ ሰይፍ አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ሁኔታ ዳዊት በወንጭፍና በድንጋይ ብቻ ፍልስጥኤማዊውን አሸነፈው፤ በእጁም ሰይፍ ሳይዝ ፍልስጥኤማዊውን መታው፤ ገደለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ሁኔታ ዳዊት በወንጭፍና በድንጋይ ብቻ ፍልስጥኤማዊውን አሸነፈው፤ በእጁም ሰይፍ ሳይዝ ፍልስጥኤማዊውን መታው፤ ገደለውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት ዳዊት በወንጭፍና በድንጋይ ጎልያድን መትቶ በመግደል ድል አደረገ! በእጁም ሰይፍ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው፥ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለ፥ በዳዊትም እጅ ሰይፍ አልነበረም። |
ከእርሱም በኋላ የሐናት ልጅ ሴሜጋር ተነሣ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ስድስት መቶ ሰው በበሬ መውጊያ ገደለ፤ እርሱም ደግሞ እስራኤልን አዳነ።
ስለዚህም በማኪማስ ጦርነት ጊዜ ሰይፍና ጦር ከሳኦልና ከዮናታን ጋር በነበሩ ሕዝብ ሁሉ እጅ አልተገኘም፤ ብቻ በሳኦልና በልጁ በዮናታን ዘንድ ተገኘ።
ዳዊትንም ሰይፉን በልብሱ ላይ አስታጠቀው፤ ዳዊትም አንድና ሁለት ጊዜ ሲራመድ ደከመ። ዳዊትም ሳኦልን፥ “አለመድሁምና በዚህ መሄድ አልችልም” አለው። ከላዩም አወለቁለት።
ዳዊትም እጁን ወደ ኮሮጆው አግብቶ አንድ ድንጋይ ወሰደ፤ ወነጨፈውም፤ ፍልስጥኤማዊውንም ግንባሩን መታው፤ ድንጋዩም ጥሩሩን ዘልቆ በግንባሩ ተቀረቀረ፤ እርሱም በምድር ላይ በፊቱ ተደፋ።
ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፤ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፤ ገደለውም፤ ራሱንም ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ዋናቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ።
ነፍሱንም በእጁ ጥሎ ፍልስጥኤማዊዉን ገደለ፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ እስራኤልም ሁሉ አይተው ደስ አላቸው፤ በከንቱ ዳዊትን ትገድለው ዘንድ ስለምን በንጹሕ ደም ላይ ትበድላለህ?”
ካህኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመጐናጸፊያ ተጠቅልላ አለች፤ የምትወስዳት ከሆነ ውሰዳት፤ ከእርስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለምና” አለው። ዳዊትም፥ “ከእርስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እርስዋን ስጠኝ” አለው። እርሱም ሰጠው።