በራሱም የናስ ቍር ደፍቶ ነበር፤ ጥሩርም ለብሶ ነበር፤ የጥሩሩም ሚዛን አምስት ሺህ ሰቅል ናስና ብረት ነበረ።
እርሱም ከናስ የተሠራ የራስ ቍር ደፍቶ፣ ክብደቱ ዐምስት ሺሕ ሰቅል የሆነ የናስ ጥሩር ለብሶ ነበር።
እርሱም ከናስ የተሠራ የናስ ቁር ደፍቶ፥ ክብደቱ አምስት ሺህ ሰቅል የሆነ የናሐስ ጥሩርም ለብሶ ነበር።
ከነሐስ የተሠራና ክብደቱ ኀምሳ ሰባት ኪሎ የሚሆን ጥሩርና ከነሐስ የተሠራ የራስ ቊር ነበረው።
በራሱም የናስ ቁር ደፍቶ ነበር፥ ጥሩርም ለብሶ ነበር፥ የጥሩሩም ሚዛን አምስት ሺህ ሰቅል ናስ ነበረ።
ፈረሰኞች ሆይ፥ ፈረሶችን ጫኑና ውጡ፤ ራስ ቍርንም ደፍታችሁ ቁሙ፤ ጦርንም ሰንግሉ፤ ጥሩርንም ልበሱ።
የመዳንንም የራስ ቍር በራሳችሁ ላይ ጫኑ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ ያዙ፤ ይኸውም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ከፍልስጥኤማውያንም ሰፈር የጌት ሰው ጎልያድ፥ ቁመቱም ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ፥ ኀይለኛ ሰው መጣ።
በእግሮቹም ላይ የናስ ገምባሌ ነበረ፤ የናስም ጭሬ በትከሻው ላይ ነበረ።