La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 17:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም እጁን ወደ ኮሮ​ጆው አግ​ብቶ አንድ ድን​ጋይ ወሰደ፤ ወነ​ጨ​ፈ​ውም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ግን​ባ​ሩን መታው፤ ድን​ጋ​ዩም ጥሩ​ሩን ዘልቆ በግ​ን​ባሩ ተቀ​ረ​ቀረ፤ እር​ሱም በም​ድር ላይ በፊቱ ተደፋ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እጁንም ወደ ኰረጆው በመስደድ አንድ ድንጋይ አውጥቶ ወነጨፈው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ግንባሩ ላይ መታው። ድንጋዩም ግንባሩ ውስጥ ገብቶ ተቀረቀረ፤ ፍልስጥኤማዊውም በግምባሩ ተደፋ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እጁንም ወደ ኮሮጆው በመስደድ አንድ ድንጋይ አውጥቶ ወነጨፈው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ግንባሩ ላይ መታው። ድንጋዩም ግንባሩ ውስጥ ገብቶ ተቀረቀረ፤ በግምባሩም ምድር ላይ ተደፋ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እጁንም ወደ ኮረጆው ከቶ አንዲት ድንጋይ በማውጣት በጎልያድ ላይ ወነጨፈ፤ ድንጋዩም ግንባሩን በጥርቆ ወደ ራስ ቅሉ ገባ፤ ጎልያድም በምድር ላይ በግንባሩ ተደፋ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም እጁን ወደ ኮረጆው አግብቶ አንድ ድንጋይ ወሰደ፥ ወነጨፈውም፥ ፍልስጥኤማዊውንም ግምባሩን መታ፥ ድንጋዩም በግምባሩ ተቀረቀረ፥ እርሱም በምድር ላይ በፊቱ ተደፋ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 17:49
6 Referencias Cruzadas  

አንድ ሰውም ቀስ​ቱን ድን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በሳ​ን​ባ​ውና በደ​ረቱ መካ​ከል ወጋው፤ ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “መል​ሰህ ንዳ፤ ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና ከሰ​ልፍ ውስጥ አው​ጣኝ” አለው።


ኢዩም በእጁ ቀስ​ቱን ለጠጠ፤ ኢዮ​ራ​ም​ንም በጫ​ን​ቃው መካ​ከል ወጋው ፤ ፍላ​ጻ​ውም በልቡ አለፈ፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ውስጥ በጕ​ል​በቱ ላይ ወደቀ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ተነ​ሥቶ ዳዊ​ትን ሊገ​ና​ኘው በቀ​ረበ ጊዜ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ሊገ​ና​ኘው ወደ ሰልፉ ሮጠ።


ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን በወ​ን​ጭ​ፍና በድ​ን​ጋይ አሸ​ነ​ፈው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም መትቶ ገደለ ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ ሰይፍ አል​ነ​በ​ረም።


ነፍ​ሱ​ንም በእጁ ጥሎ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ገደለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አይ​ተው ደስ አላ​ቸው፤ በከ​ንቱ ዳዊ​ትን ትገ​ድ​ለው ዘንድ ስለ​ምን በን​ጹሕ ደም ላይ ትበ​ድ​ላ​ለህ?”