የኢዮሔል ልጅ ሩጻፋም ማቅ ወስዳ ከመከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰማይ እስኪዘንብ ድረስ በድንጋይ ላይ ዘረጋችው፤ በቀንም የሰማይ ወፎች፥ በሌሊትም የዱር አራዊት ያርፉባቸው ዘንድ አልተወችም።
1 ሳሙኤል 17:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፥ “ወደ እኔ ና፤ ሥጋህንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣቸዋለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማዊውም፣ “እስኪ ወደኔ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞሮችና፣ ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ዳዊትን፥ “እስቲ ወደኔ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞሮችና፥ ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም “ወዲህ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞራዎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፦ ወደ እኔ ና፥ ሥጋህንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ አለው። |
የኢዮሔል ልጅ ሩጻፋም ማቅ ወስዳ ከመከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰማይ እስኪዘንብ ድረስ በድንጋይ ላይ ዘረጋችው፤ በቀንም የሰማይ ወፎች፥ በሌሊትም የዱር አራዊት ያርፉባቸው ዘንድ አልተወችም።
ለጠላቶቻቸው እጅ፥ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢሮስን አለቃ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርትዋል፥ አንተ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ እግዚአብሔርም በባሕር መካከል እንዲቀመጥ እኔም ተቀምጫለሁ ብለሃልና፤ አንተ ሰው ስትሆን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ እግዚአብሔር አይደለህም።
አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፤ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ “መጥታችሁ የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር እራት ተከማቹ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
የሰፈሩም ሰዎች፦ ዮናታንንና ጋሻ ጃግሬውን “ወደ እኛ ውጡ፤ አንድ ነገርንም እንነግራችኋለን” አሉ። ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን “እግዚአብሔር በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ተከተለኝ” አለው።
እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እመታህማለሁ፤ ራስህንም ከአንተ እቈርጠዋለሁ፤ ሬሳህንና የፍልስጥኤማውያንንም ሠራዊት ሬሶች ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ዛሬ እሰጣለሁ። ምድር ሁሉ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር እንዳለ ያውቃሉ፤