1 ሳሙኤል 17:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእሴይም ሦስቱ ታላላቆች ልጆቹ ሳኦልን ተከትለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፤ ወደ ሰልፉም የሄዱት የሦስቱ ልጆች ስም ይህ ነበረ፤ ታላቁ ኤልያብ፥ ሁለተኛውም አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሣማዕ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስቱ የእሴይ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነት ሄደው ነበር፤ እነርሱም ታላቁ ኤልያብ፣ ሁለተኛው አሚናዳብ፣ ሦስተኛውም ሣማ ይባላሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦስቱ የእሴይ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነት ሄደው ነበር፤ እነርሱም ታላቁ ኤሊአብ፥ ሁለተኛው አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሻማ ይባላሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስቱ ታላላቅ ልጆቹም ከሳኦል ጋር ወደ ጦርነት ዘምተው ነበር፤ እነርሱም በኲሩ ኤሊአብ፥ ሁለተኛው አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሻማ ተብለው ይጠሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእሴይም ሦስቱ ታላላቆች ልጆቹ ሳኦልን ተከትለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፥ ወደ ሰልፉም የሄዱት የሦስቱ ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፥ ታላቁ ኤልያብ ሁለተኛውም አሚናዳብ ሦስተኛውም ሣማ ነበረ። |
የዳዊትም ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ መልሶ እንዲህ አለው፥ “ጌታዬ ጐልማሶቹ የንጉሡ ልጆች ሁሉ እንደ ሞቱ አያስብ፤ እኅቱን ትዕማርን በግድ ካስነወራት ጀምሮ በአቤሴሎም ዘንድ የተቈረጠ ነገር ነበረና የሞተ አምኖን ብቻ ነው።
ታላቅ ወንድሙም ኤልያብ ከሰዎች ጋር ሲነጋገር ሰማ፤ ኤልያብም በዳዊት ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂቶች በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውሃቸው? እኔ ኵራትህንና የልብህን ክፋት አውቃለሁና ሰልፉን ለማየት መጥተሃል” አለው።