1 ሳሙኤል 16:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፥ “በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እዚያ በደረሱ ጊዜም፣ ሳሙኤል ኤልያብን አይቶ፣ “በርግጥ እግዚአብሔር የቀባው ሰው እነሆ፤ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል” ብሎ ዐሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚያ በደረሱ ጊዜም፥ ሳሙኤል ኤልያብን አይቶ፥ “በእርግጥ ጌታ የቀባው ሰው እነሆ፤ በጌታ ፊት ቆሞአል” ብሎ አሰበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም በደረሱ ጊዜ ሳሙኤል ኤሊአብ ተብሎ የሚጠራውን የእሴይን ልጅ አይቶ “በእግዚአብሔር ፊት የቆመው ይህ ሰው በእርግጥ ለንጉሥነት የተመረጠ ነው” ሲል አሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው አለ። |
ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ የዘለዓለም ንጉሥ እሆን ዘንድ ከአባቴ ቤት ሁሉ መርጦኛል፤ ይሁዳንም አለቃ ይሆን ዘንድ መርጦታል፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት መርጦአል፤ ከአባቴም ልጆች መካከል በእስራኤል ሁሉ ላይ ያነግሠኝ ዘንድ እኔን ሊመርጠኝ ወደደ።
ሮብዓምም የዳዊትን ልጅ የኢያሪሙትን ሴት ልጅ ሞላትን አገባ፤ እናቷም የእሴይ ልጅ የኤልያብ ልጅ አቢካኤል ነበረች።
ዛብሄልንና ስልማናን፥ “በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” አላቸው፤ እነርሱም፥ “እንዳንተ ያሉ ነበሩ፤ አንተንም ይመስሉ ነበር፤ መልካቸውም እንደ ነገሥት ልጆች መልክ ነበረ” ብለው መለሱለት።
የእሴይም ሦስቱ ታላላቆች ልጆቹ ሳኦልን ተከትለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፤ ወደ ሰልፉም የሄዱት የሦስቱ ልጆች ስም ይህ ነበረ፤ ታላቁ ኤልያብ፥ ሁለተኛውም አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሣማዕ ነበረ።