ይኸውም ከሶርያ ከሞዓብና ከአሞን ልጆች፥ ከፍልስጥኤማውያንም፥ ከአማሌቅም፥ ከረአብም ልጅ ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር ምርኮ ያመጣው ነው።
1 ሳሙኤል 15:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማሌቅንም ንጉሥ አጋግን በሕይወቱ ማረከው፤ የኢያሬምንም ሕዝብ ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዐማሌቅ ንጉሥ የነበረውን አጋግን በሕይወት ማርኮ፥ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ፈጀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአማሌቅንም ንጉሥ አጋግን በሕይወቱ ማረከው፥ ሕዝቡንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። |
ይኸውም ከሶርያ ከሞዓብና ከአሞን ልጆች፥ ከፍልስጥኤማውያንም፥ ከአማሌቅም፥ ከረአብም ልጅ ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር ምርኮ ያመጣው ነው።
እርስዋንም፥ ንጉሥዋንም፥ ከተሞችዋንም ያዙ፤ በሰይፍም ስለት መቱአቸው፤ በእነርሱም ውስጥ ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽመው አጠፉ፤ ማንንም አላስቀረም፤ በኬብሮንና በንጉሥዋም እንዳደረገው እንዲሁ በዳቤርና በንጉሥዋ አደረገ።
የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን መንግሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ ያዘ፤ በሰይፍም መታቸው፤ ፈጽሞም አጠፋቸው።
ሳኦልም ሳሙኤልን፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ስለሰማሁ፥ እግዚአብሔር በላከኝ መንገድ ሄጃለሁ፤ የአማሌቅን ንጉሥ አጋግንም አምጥቻለሁ፤ አማሌቃውያንንም ፈጽሜ አጥፍቻለሁ።
አሁንም ሄደህ አማሌቅንና ኢያሬምን ምታ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ ከእነርሱም የምታድነው የለም። አጥፋቸው፤ መከራም አጽናባቸው፤ የእነርሱ የሆነውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያቸውም፤ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን፥ ብላቴናውንና ሕፃኑን፥ በሬውንና በጉን፥ ግመሉንና አህያውን ግደል።”
የካህናቱንም ከተማ ኖብን በሰይፍ ስለት መታ፤ ወንዶችንና ሴቶችንም፥ ብላቴኖችንና ጡት የሚጠቡትን፥ በሬዎችንና አህዮችንም፥ በጎችንም በሰይፍ ስለት ገደለ።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ሴቄላቅ በገቡ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በአዜብ በሰቄላቅም ላይ ዘምተው ነበር፤ ሴቄላቅንም መትተው በእሳት አቃጥለዋት ነበር፥