አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ጽንዕ የአንተ ነው፤ ነገሥታቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊትህ ይደነግጣሉ።
1 ሳሙኤል 15:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል ለሁለት ይከፈላል፤ ከእንግዲህም አይሰበሰብም፤ እግዚአብሔርም እንደ ሰው የሚጸጸት አይደለምና አይጸጸትም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ክብር የሆነው እግዚአብሔር አይዋሽም፤ አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለምና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ክብር የሆነው እርሱ አይዋሽም፤ አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ክብር የሆነ እግዚአብሔር አያብልም፤ ሐሳቡንም አይለውጥም፤ እርሱ እንደ ሰው ስላልሆነ ሐሳቡን አይለውጥም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ኃይል እንደ ሰው የሚጸጸት አይደለምና አይዋሽም አይጸጸትምም አለው። |
አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ጽንዕ የአንተ ነው፤ ነገሥታቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊትህ ይደነግጣሉ።
እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እመጣለሁ፤ እኔም አደርገዋለሁ፤ አልተውም፤ አልራራም፤ አልጸጸትም፤ እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽም እፈርድብሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ስለዚህ የሰውን ደም እንደ አፈሰስሽ እኔ እፈርድብሻለሁ፤ እንደ ኀጢአትሽም ተበቅዬ አጠፋሻለሁ፤ ስምሽም ጐሰቈለ፥ ብዙ ኀዘንንም ታዝኛለሽ።”
እግዚአብሔርም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ይራራል፤ የእስራኤልንም ልጆች ያጸናል።
እግዚአብሔር እንደ ሰው የሚታለል አይደለም። እንደ ሰው ልጅም የሚዛትበት አይደለም፤ እርሱ ያለውን አያደርገውምን? አይናገረውምን? አይፈጽመውምን?
እርሱም፥ “ጸጋዬ ይበቃሀል፤ ኀይልስ በደዌ ያልቃል” አለኝ፤ የክርስቶስም ኀይል በእኔ ላይ ያድር ዘንድ በመከራዬ ልመካ ወደድሁ።
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።
በመሐላ የሾመውን ግን፥ “እግዚአብሔር ማለ፥ አይጸጸትምም፤ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዘለዓለም ካህን ነህ” አለው።