La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮና​ታ​ንም በኮ​ረ​ብ​ታው የነ​በ​ሩ​ትን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ መታ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ያን ሰሙ፤ ሳኦ​ልም፦ እስ​ራ​ኤል ይስሙ ብሎ በሀ​ገሩ ሁሉ ቀንደ መለ​ከት ነፋ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮናታን ጌባዕ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፣ “ዕብራውያን ይስሙ!” በማለት በምድሪቱ ሁሉ መለከት አስነፋ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮናታን ጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፥ “ዕብራውያን ይስሙት!” በማለት በሀገሩ ሁሉ መለከት አስነፋ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮናታን ጌባዕ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጣለ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ይህን ወሬ ሰሙ፤ ሳኦልም መልእክተኞችን ልኮ በሀገሩ ሁሉ እምቢልታ በማስነፋት ዕብራውያን ለጦርነት ጠራ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮናታንም በናሲብ ውስጥ የነበረውን የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መታ፥ ፍልስጥኤማውያንም ያን ሰሙ፥ ሳኦልም፦ ዕብራውያን ይስሙ ብሎ በአገሩ ሁሉ ቀንደ መለከት ነፋ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 13:3
12 Referencias Cruzadas  

ኢዮ​አ​ብም ቀንደ መለ​ከት ነፋ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ተመ​ለሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ እስ​ራ​ኤ​ልን አላ​ሳ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውም፤ ደግ​መ​ውም አል​ተ​ዋ​ጉም።


በዚ​ያም አንድ ብን​ያ​ማዊ የቢ​ኮሪ ልጅ ስሙ ሳቡሄ የሚ​ባል የዐ​መፅ ልጅ የሆነ ሰው ነበረ፤ እር​ሱም፥ “ከዳ​ዊት ዘንድ እድል ፋንታ የለ​ንም፦ ከእ​ሴ​ይም ልጅ ዘንድ ርስት የለ​ንም፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ድህ ወደ ድን​ኳ​ንህ ተመ​ለስ” ብሎ መለ​ከት ነፋ።


በዚያ ጊዜም ዳዊት በም​ሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በዚያ ጊዜ በቤተ ልሔም ነበረ።


በቆላ ያል​ፋል፤ ወደ አን​ጋ​ይም በደ​ረሰ ጊዜ ሬማ​ትና የሳ​ኦል ከተማ ገባ​ዖን ይፈ​ራሉ፤


ምድር ሁሉ ከጌባ ጀምሮ በኢየሩሳሌምም ደቡብ በኩል እስካለችው እስከ ሬሞን ድረስ ተለውጣ እንደ ዓረባ ትሆናለች፣ እርስዋም ከፍ ከፍ ትላለች፥ ከብንያምም በር ጀምሮ እስከ ፊተኛው በር ስፍራ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ፥ ከሐናንኤልም ግንብ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መጥመቂያ ድረስ በስፍራዋ ትኖራለች።


ቃራፋ፥ ቄፍራ፥ ሞኒ፥ ጋባህ፤ ዐሥራ ሁለቱ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ገባ​ዖ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጋቲ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤


ከዚ​ህም በኋላ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር በደ​ረሰ ጊዜ በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ራም ሀገር ቀንደ መለ​ከት ነፋ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከእ​ርሱ ጋር ከተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ወረዱ፤ እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው ሄደ።


ጌዴ​ዎ​ን​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አጸ​ናው፤ እር​ሱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ነፋ፤ አብ​ዔ​ዜ​ርም በኋ​ላው ጮኸ።


ከዚ​ያም በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ ወዳ​ለ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኮረ​ብታ ትመ​ጣ​ለህ፤ በዚ​ያም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ናሴብ አለ፤ ወደ​ዚ​ያም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በደ​ረ​ስህ ጊዜ በገ​ናና ከበሮ፥ እም​ቢ​ል​ታና መሰ​ንቆ ይዘው ትን​ቢት እየ​ተ​ና​ገሩ ከኰ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ የሚ​ወ​ርዱ የነ​ቢ​ያ​ትን ጉባኤ ታገ​ኛ​ለህ።


ሳኦ​ልና ልጁ ዮና​ታ​ንም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ተቀ​ም​ጠው አለ​ቀሱ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ።