ኢየሩሳሌምንም አጠፋት፥ አለቆቹንም ሁሉ፥ ጽኑዓኑንና ኀያላኑን ሁሉ፥ ጠራቢዎቹንም ሁሉ፥ ብረት ሠራተኞቹንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምርኮኞችን ሁሉ አፈለሰ፤ ከሀገሩ ድሆች በቀር ማንም አልቀረም።
1 ሳሙኤል 13:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም፥ “ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ” ብለው ነበርና በእስራኤል ምድር ሁሉ ብረት ሠሪ አልተገኘም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን፣ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር፣ በመላው የእስራኤል ምድር የእጅ ጥበብ ባለሙያ አልተገኘም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመላው የእስራኤል ምድር ብረት አቅልጦ ሠሪ አይገኝም ነበር፤ ምክንያቱም ፍልስጥኤማውያን፥ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ ፍልስጥኤማውያን ቊጥጥር ያደርጉባቸው ስለ ነበር በዚያን ዘመን በእስራኤል ብረት አቅልጠው የሚሠሩ ጠቢባን አልነበሩም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም፦ ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ ብለው ነበርና በእስርኤል ምድር ሁሉ ብረተ ሠሪ አልተገኘም። |
ኢየሩሳሌምንም አጠፋት፥ አለቆቹንም ሁሉ፥ ጽኑዓኑንና ኀያላኑን ሁሉ፥ ጠራቢዎቹንም ሁሉ፥ ብረት ሠራተኞቹንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምርኮኞችን ሁሉ አፈለሰ፤ ከሀገሩ ድሆች በቀር ማንም አልቀረም።
እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ እንደሚያናፋ፥ ለሥራውም መሣሪያ እንደሚያወጣ ብረት ሠሪ የፈጠርሁሽ አይደለም፤ እኔ ግን ለመልካም ፈጠርሁሽ እንጂ ለጥፋት አይደለም።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች፥ ብልሃተኞችንና እስረኞችን፥ ጓደኞቻቸውንም ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ከአፈለሳቸው በኋላ፥ እነሆ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ቅርጫቶችን አሳየኝ።
ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያንና እቴጌዪቱ፥ ጃንደረቦቹም፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌምም አለቆች ነጻዎችና እሥረኞች፥ ብልሃተኞችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው።
እስራኤልም ሁሉ ማረሻውንና ማጭዱን፥ መጥረቢያውንና መቈፈሪያውን ይስሉ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርዱ ነበር።