በነጋውም ሙሴ ለሕዝቡ፥ “እናንተ ታላቅ በደል ሠርታችኋል፤ አሁንም አስተሰርይላችሁ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ፤” አላቸው።
1 ሳሙኤል 12:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የስንዴ መከር ዛሬ አይደለምን? ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ እርሱም ነጐድጓድንና ዝናብን ይልካል፤ እናንተም ንጉሥ በመለመናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ያደረጋችሁት ክፋት ታላቅ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ፤ ታያላችሁም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን የስንዴ መከር ጊዜ አይደለምን? እኔ ነጐድጓድና ዝናብ እንዲልክ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት የቱን ያህል የከፋ ድርጊት እንደፈጸማችሁ ያን ጊዜ ታውቃላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን የስንዴ መከር ጊዜ አይደለምን? እኔ ነጐድጓድና ዝናብ እንዲልክ ወደ ጌታ እጮኻለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ በጌታ ፊት የቱን ያህል የከፋ ድርጊት እንደፈጸማችሁ ያንጊዜ ታውቃላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ አሁን እንደምታውቁት የፀሐይ ሙቀት የበዛበት የስንዴ መከር ወራት አይደለምን? ነገር ግን እኔ አሁን እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድና ዝናብ ይልካል፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ንጉሥ እንዲያነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ ምክንያት በደል በመሥራት እግዚአብሔርን ያሳዘናችሁ መሆናችሁን ታረጋግጣላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የስንዴ መከር ዛሬ አይደለምን? ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፥ እርሱም ነጎድጓድና ዝናብ ይልካል፥ እናንተም ንጉሥ በመለመናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ያደረጋችሁት ክፋት ታላቅ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ ታያላችሁም። |
በነጋውም ሙሴ ለሕዝቡ፥ “እናንተ ታላቅ በደል ሠርታችኋል፤ አሁንም አስተሰርይላችሁ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ፤” አላቸው።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ እነዚህን ሕዝቦች ከፊቴ አባርራቸው፤ ይውጡ።
ያን ጊዜም እግዚአብሔር በእስራኤል ልጆች እጅ አሞሬዎናውያንን አሳልፎ ሰጠ፤ እርሱ በገባዖን እነርሱን ባጠፋበት፥ እነርሱም ከእስራኤል ልጆች ፊት በጠፉበት ቀን ኢያሱ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ፤ እንዲህም አለ፥ “በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፤ በኢሎንም ሸለቆ ጨረቃ፤”
ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፥ “ንጉሥ በመለመናችን በኀጢአታችን ሁሉ ላይ ይህን ክፋት ጨምረናልና እንዳንሞት ስለ ባሪያዎችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት።
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ያደክማቸዋል፤ እግዚአብሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበበኛ በጥበቡ አይመካ፤ ኀይለኛም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይመካ፤ የሚመካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግዚአብሔርን በማወቅና በማስተዋል፤ በምድርም መካከል ፍርድንና እውነትን በማድረግ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አንጐደጐደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሦቻችንም ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፥ “በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን ናቁ እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ።